መነሻ / የቢዝነስ ዜና / የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር 12 መንገዶች ሊያሠራ ነው

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር 12 መንገዶች ሊያሠራ ነው

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር ወጪ 12 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ፊርማ ከተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማ የተከናወነባቸው 12ቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በድምሩ 825.23 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው መሆኑም ታውቋል።

ለግንባታው ከሚያስፈልገው ወጪ መካከል የአሥሩ መንገዶች በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ ሲሆን፣ ሁለቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው ተብሏል።

የውል ስምምነቱን ከፈረሙት የሥራ ተቋራጮች መካከል ስድስቱ አገር በቀል ድርጅቶች፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ዓለም አቀፍ የውጭ ተቋራጮች መሆናቸው ተመልክቷል።

መንገዶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ እንደየርዝመታቸው አንድ ዓመት ከአምስት ወራት እስከ አራት ዓመታት እንደሚወስድ ተገልጿል። መንገዶቹ በገጠር እስከ 10 ሜትር ስፋት ሲኖራቸው፣ በከተማ ደግሞ ከአሥር ሜትር በላይ ስፋት ይኖራቸዋል፤ እንዲሁም በመንገዶቹ ላይ ድልድዮች እና ሌሎች ተያያዥ ግንባታዎች ይኖራሉ።


የዜና ምንጭ፦ ዋልታ

ይህንንም ይመልከቱ

artisanal-miner

የሮያሊቲ ክፍያ ለባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሙሉ በሙሉ ተነሳላቸው

በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረው የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በክልሎች …