በየወረዳው በሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት መስጫ “አንድ ማዕከል” ሥር፣ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሚገኝ ሲሆን፣ ሁለት ዓይነት የብድር አገልግሎት ይሰጣል።
ብድር ለመጠየቅ ምን ምን ማሟላት ያስፈልጋል?
ለአዲስ ኢንተርፕራይዞች፡-
- ሕጋዊ ሰውነት ማግኘት
- (ዋና ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ፣ በንግድ ሕጉ ሥር ከተዘረዘሩት ዘርፎች በአንዱ መመዝገብ፣ እንዲሁም በጋራ ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማቅረብ)
- የንግድ ዕቅድ ማቅረብ
ለነባር ኢንተርፕራይዞች፡-
- የሃብት መግለጫ (financial statement)
- የታደሰ የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ
- የመሥሪያ ቦታ ከመንግሥት ከተሰጣቸው ይህንን የሚገልጽ ማስረጃ
- የፈጠሩት የሥራ ዕድል መጠን
- በብድር መጠየቂያ (proposal) ላይ ስለሚፈጥሩት ተጨማሪ የሥራ ዕድል ማብራሪያ
ምን ምን ዓይነት ብድሮች ማግኘት ይቻላል?
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ ሁለት ዓይነት የብድር አገልግሎት ይሰጣል።
- መደበኛ ብድር
መደበኛ ብድር የሚሰጣቸው፡-- ለ6 ወራት ቅድመ ቁጠባ ያደረጉ፣
- ለብድር ከሚጠይቁት ገንዘብ 20 ከመቶ የሚሆነው የቆጠቡ፣ እንዲሁም
- እንደ ብድሩ መጠን መያዣ ንብረት ወይም ተያዥ የሚሆን ሰው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተዘዋዋሪ ብድር
ተዘዋዋሪ ብድር፣ በኢንተርፕራይዙ መስራቾች መሃል አንዳቸው ለሌላቸው ዋስ በመሆን (በጠለፋ ዋስትና) የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ብድር የሚያዝ ንብረት ሳይኖር ሊሰጥ የሚችል ነው። ተዘዋዋሪ ብድር የሚሰጣቸው፡-- ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወይም
- ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ናቸው።