መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / አብያት የኢንጂነሪንግ እና አርክቴክቸር አማካሪ
abyat-logo

አብያት የኢንጂነሪንግ እና አርክቴክቸር አማካሪ

አብያት ኮንሰልቲንግ የተመሠረተው በአቶ ናትናኤል እና በሶስት መሥራች አባላት 2012 ዓ.ም ላይ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኢንጂነሪንግ እና አርክቴክቸር ሥራዎች የማማከር አገልግሎት ይሠጣል።

architectureየሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የኮንስትራክሽን ላይ ሥራ እና የማማከር አገልግሎት
  • የአርክቴክቸራል ዲዛይን ሥራ ማማከር
  • የስትራክቸራል ዲዛይን የማማከር አገልግሎት
  • የሳኒተሪ ዲዛይን ሥራ የማማከር አገልግሎት
  • ኤሌክትሪካል ሥራዎችን የማማከር አገልግሎት
  • የኢንቲርየር ዲዛይን ሥራ የማማከር አገልግሎት
  • 3ዲ ሞዴሊንግ እና አኒሜሽን ሥራ
  • አዝ ቢልት (As Built) ዶክሜንቴሽን መሥራት (በተለያየ ምክንያት ካርታ ለጠፋባቸው ንብረቶች ካርታ ሲጠፋ እንደ አዲስ ለክቶ መሥራት)

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ናትናኤል አብያት ኮንሰሊትንግ ድርጅት ን ከመመሥረታቸው በፊት በትምህርት ቤት እያሉ ከጓደኞቻቸው ጋር ሆነው የራሳቸው ድርጅት የመመሥረት ሃሳብ ነበራቸው። ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በድራፍቲንግ፣ አርክቴክቸር፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና በኤሌክትሪካል የትምህርት ዘርፍ የተማሩ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ስለነበሩ በኮንሰልቲንግ ብንሠማራ ያዋጣናል ብለው ድርጅቱን መሥርተዋል። ለዚህ መሳካት ደግሞ በሁሉም መሥራች አባላት ዘንድ የመሥራት ፍላጎት ስለነበር ወደ ዘርፉ የገቡት። እንዲሁም ከነሱ በፊት ሥራውን የጀመሩ ጓደኞቻቸው ስለነበሩ ከእነሱ መረጃ በመጠየቅ እና በማጣራት ስህተት እንዳይፈጠር እየተጋገዙ እየሠሩ ይገኛሉ።

ድርጅቱ የሚሠጠውን ማንኛውንም ሥራ በተባለው የጊዜ ገደብ የማጠናቀቅ አቅም አለው። ሆኖም ሥራዎች አንዳንድ ጊዜ በበጀት አጥረት አማካኝነት ሊራዘሙ የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል። የድርጅቱ የመሥራት አቅም እንደ ሥራው አይነት እና በጀቱ  የሚለያይ ቢሆን ትንሹ የሚባለው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ማጠናቀቅ ይችላል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሰው በሰው እና ሁሉም አባላት በግል ከሚያገኟቸው ሰዎች ጋር በመነጋገር እንዲሁም ጨረታዎችን በመከታተል ነው። የግል ድርጅቶች ድፍረው የማሠራት ልምዱ ገና ነው፤ ስለዚህ ለጊዜው ጨረታዎችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮቪድ ጊዜ ኮንትራት ይዘው እየሠሯቸው የነበሩ ሁለት ሥራዎች በሁለት ክፍለ ከተማ ነበሩ። ግን በተባለው ጊዜ ለማጠናቀቅ አልተቻለም ነበር፤ ምክንያቱም በጀት በተለያዩ ነገሮች ላይ እየዋለ ስለነበር በአራት ወር የሚያልቅ ሥራ ከዓመት በላይ ሊጓተት ችሏል።  ከዛም በኋላ አዲስ ሥራ የማግኘት አድሉ አልነበረም። አዲስ ሥራ አግኝቶ የመሥራት እድል በጣም ቀንሶ ነበር።

ምክር እና እቅድ

ማንም ሰው ወደዚህ የሥራ መስክ ሲገባ ሥራውን ማወቅ ግዴታ ነው። አንዳንድ ሰዎች ጋር ገንዘብ ስላላቸው ብቻ እሠራዋለሁ የሚል የተሳሳተ አመለካከት ስላለ ይህ ቢሻሻል ጥሩ ነው፤ ወይም ደግሞ ባለሙያዎችን ሰብስቦ በመቅጠር ማሠራት የተሻለ አማራጭ ነው። ምክንያቱም ሥራው በዕውቀት የሚሠራ ሥራ ስለሆነ። እንደ ተጨማሪ ደግሞ ክፍለ ከተማ ያለው አሠራር ቢሻሻል ጥሩ ነው ብለው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድርጅቱ ወደ ፊት በእቅድ የያዛቸውን ፕሮጀክቶች ከከተማ መስተዳደሩ ጋር በመሆን መልማት ያለባቸው ነገሮች ለምሳሌ እንደ አረንጓዴ ስፍራ (green area) ዓይነት ሥራዎችን ነድፎ አዘጋጅቷል።  እነሱን የማስቀጠል እቅድ አለው።

እንደ ተጨማሪ ደግሞ ”2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት ተጠቅመን ጨረታ እየተሳተፍን ነው። 2merkato.com ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ከግል መሥርያ ቤቶች ጋር አብሮ ሥራ መሥራት የሚቻልበትን መንገድ ቢያመቻች ጥሩ ነው። ለምሳሌ ኮንሰልቲንግ የሚሠሩ ሰዎችን መርጦ ሌሎች ዘርፎችንም እንዲሁ መርጦ ሥራዎችን ማሠራት የሚቻልበትን መንገድ ቢያመቻች ጥሩ ነው” ብለው ሃሳባቸውን አክለዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …