መነሻ / የቢዝነስ ዜና / አዲስ የአኩሪ አተር ፕሮቲንና ዘይት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ የአኩሪ አተር ፕሮቲንና ዘይት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ሪችላንድ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነባው የአኩሪ አተር ፕሮቲን እና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ሥራውን ጀመረ።

የፋብሪካውን ሥራ መጀመር “ትዊት” ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ 61 ሚሊየን 680 ሺህ ዶላር ለአገር እንደሚያስገኝ ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ፋብሪካው ለአገር ውስጥ ፍጆታ 22 ሚሊየን 500 ሺህ ሊትር ዘይት [በዓመት] እንደሚያመርት ተገልጿል።

ፓርክ በ991,247,000 ብር ወጭ የገነባው የአኩሬ አተር ፕሮቲንና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ስራውን ጀመረ:: በሙሉ አቅሙ ሲያመርትም ከኤክስፖርት 61,680,000$ ያስገኛል ለሀገር ውስጥ 22,500,000 ሊትር ዘይት ያመርታል::

ለፋብሪካው 80 በመቶ የመሥራት አቅሙ ማምረት ሲጀምር፣ እስከ 1 ሚሊዮን 500 ሺህ ኩንታል አኩሪ አተር በግብዓትነት እንደሚጠቀም የፋብሪካው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አውደው ነግረውኛል ሲልም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጨምሮ ዘግቧል። ከዚህ ግብዓትም 80 በመቶ የሚሆነውን በዓመት 1 ሚሊየን 200 ሺህ ኩንታል የአኩሪ አተር ፕሮቲን ዱቄት ለማምረት እንደሚጠቀምበት ተወስቷል።


የከፍታን የቴሌግራም ቻነል በመቀላቀል ዘርፈ ብዙ የቢዝነስ መረጃ ያግኙ፡- https://t.me/KeftaPortal

ይህንንም ይመልከቱ

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት …