መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ገነት ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች

ገነት ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች

ገነት ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በወ/ሮ እመቤት ሽብሩ እና ሦስት አባላት ነው።ድርጅቱ በልደታ ክፍለ ከተማ ሥር የተመሠረተ ቢሆንም በጊዜው ብዙ ባዛር ልደታ ክ/ከተማ ባለመኖሩ ከልደታ ቦሌ ክ/ከተማ እየመጡ ነበር ባዛር የሚገለገሉት። ይህ ችግር ለማስወገድ ከቦሌ ክ/ከተማ ጋር በመነጋገር ወደ ቦሌ ክ/ከተማ ሊዘዋወሩ ችለዋል። ይህም ለድርጅቱ ሥራ መጠናከር ትልቅ አስተዋጽዖ አንዳበረከተ ወ/ሮ እመቤት ገልጸዋል።

 

ድርጅቱ ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል

 • ጃኬት
 • ቦርሳ
 • ቀበቶ
 • የላፕቶፕ ቦርሳዎች
 • ቀለል ያሉ ጫማዎች
 • የቁልፍ መያዣ

ምሥረታ፣ ዕድገት፣ ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ድርጅቱ አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ያመርታል። ድርጅቱ ጠንክሮ በመሥራቱ ተጨማሪ አንድ ማሽን በመግዛት እና ሁለት የማሳያ ሱቆችን በመገናኛ እና በልደታ ፍርድ ቤት አካባቢ መክፈት ችሏል። በሁለት ሺህ ብር ካፒታል የተመሠረተ ድርጅት በአሁኑ ጊዜ ሁለት መቶ ሺህ ብር ካፒታል አለው። በቅርቡ ደግሞ ደግሞ ምርቶቹን ወደ ውጭ ሃገር ገበያ ለመላክ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል። ድርጀቱ በቀን መቶ ቦርሳዎችን በጥራት የማምረት አቅም አለው።

ድርጅቱ የኑሮ ውድነት ታሳቢ በማድረግ የሚያመርታቸውን ምርቶች ቀለል ባለ መልኩ የማኅበረሰቡን የመክፈል አቅም አገናዝቦ ነው የሚያመርተው እና የሚሸጠው።

ለምሳሌ

 • የሴቶች ቦርሳ ከስድስት መቶ ሀምሳ ብር እስከ ሰባት መቶ ብር ለገበያ ያቀርባል
 • የላፖፕቶፕ መያዣ በዘጠኝ መቶ ብር ለገበያ ያቀርባል
 • አነስ ያሉ የቆዳ ቦርሳዎች ሰበባት መቶ ብር ለገበያ ያቀርባል
 • የወንድ የኪስ ቦርሳዎች ከመቶ ሀምሳ እስከ መቶ ሰምንያ ብር ለገበያ ያቀርባል
 • ቀበቶ ከመቶ ሀምሳ ብር እስከ መቶ ሰማንያ ብር ለገበያ ያቀርባል

ወ/ሮ እመቤት ድርጅታቸውን ከመመሥረታቸው በፊት ለስድስት ወር የኅትመት ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል፤ በዚህም ጊዜ ደንበኛ እንዴት መቀበል አንዳለባቸው ጥሩ ልምድ አካብተዋል። የቆዳ ሥራ የጀመሩት ለሥራ ወደ ውጭ ሄደው በነበረት ወቅት በቴሌቪዥን ሲከታተሉ ሠርተው የተሸለሙ ሰዎችን ታሪክ ካዩ በሁዋላ እንደሆነም አስረድተዋል። በመቀጠል ከጓደኞቻቸው ጋር በመመካከር እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ሰዎችን ስለሚያውቁ ከነሱ ጋር ከተመካከሩ በኋላ በቆዳ ሥራ ላይ የሚሰጥ የዐሥራ አምስት ቀን ሥልጠና ከወረዳ እንዲሁም የሰባት ወር ሥልጠና በግላቸው ከሠለጠኑ በኋላ ነው ነው የቆዳ ሥራ የጀመሩት።

 

ድርጅቱ ሲመሠረት በአራት መሥራች አባላት እና በሁለት ሺህ ብር ካፒታል ነበር። ድርጅቱ አብዛኛው ምርት ለገበያ የሚያቀርበው (ገቢውን) የሚያገኘው ኤግዚብሽን ላይ በመሸጥ ነበር። በጊዜው ብዙ የባዛር እድሎች ስለነበሩ ሁለትም ሦስትም ቦርሳ በማምረት ባዛር ላይ በመሸጥ ትርፉን በመቆጠብ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴ ጨምሯል። ከጊዜ በኋላ ግን ባዛር እየቀነሰ መጣ። ብዙ ጊዜ ባዛር የነበረው ቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ድልድይ አካባቢ ነበር። ልደታ ብዙ ባዛር አልነበረም። ስለሆነም የቦሌ እድል ሲመጣ ወ/ሮ እመቤት ልደታ የነበራቸውን ውል ወደ ቦሌ በማዘዋወር ወደ ቦሌ ክ/ከተማ ሲሄዱ ሌሎቹ ሦስት አባላት ግን ወደ ቦሌ ሳይመጡ ቀረዋል። በአሁኑ ጊዜም ወ/ሮ እመቤት ቦሌ ክ/ከተማ የመሥሪያ ቦታ ለማግኘት ወረፋ እስከሚደረሳቸው ድረስ በቤታቸው እያመረቱ የቦሌ ክ/ከተማ ኢንተርፕራይዝ በመሆናቸው ባገኙት ቦታ፣ በተከራዩት የማሳያ ሱቅ እና በባዛሮች ላይ በመሳተፍ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ተፅዕኖ ድርጅቱ ላይ ከባድ ነበር፤ ሠራተኞች ሥራ አቁመው ነበር። ምንም እቃ የሚገዛ ሰው አልነበረም። ወ/ሮ እመቤት ደግሞ ቤታቸው ቅድስት ልደታ አብነት አካባቢ ስለነበር ርቀቱ ለአደጋው ያለውን ተጋላጭነት ስለሚጨምረው ለራሳቸውም እና ለቤተሳቸው በማሰብ ለዐሥራ አምስት ቀን ድርጅቱ ሥራ አቁሞ ነበር። የነበረውን የገበያ ችግር ለመቀነስ ማስክ ከሚያመርቱ ሰዎች ጋር በመነጋገር ከእነሱ በማምጣት እና በመሸጥ ትንሽም ቢሆን የትራንስፖርት፣ የቤት ኪራይ እና ለአንዳንድ ነገሮች ተጠቅመውበታል፤ እንዲሁም በእቁብ የቆጠቡት ይህን አስከፊ ጊዜ ለመሻገር በጣም ጠቅሟቸዋል።

ምክር እና እቅድ

አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚሰማሩ ባዛር በጣም እንዲጠቀሙ ይመክራሉ። ለአዲስ ጀማሪ ባዛር በጣም ጠቃሚ ነው፤ የነሱም ድርጅት ያደገው እና አሁንም እየተንቀሳቀሰ ያለው በባዛር ስለሆነ ባዛር እንዲጠቀሙ ይመክራሉ። ለምሳሌ አንድ አዲስ የሚጀምር ሰው አንድ ወር ቢሠራ ባዛር የሚቀጥለው ወር ላይ አራት ኪሎ አምስት ቀን ፣ መገናኛ አምስት ቀን ከዛ ደግሞ የከተማ ባዛር ሜክሲኮ ላይ ምርቱን ቢሸጥ ከዛም የሚያስፈልገውን እቃ ገዝቶ ሌላውን በመቆጠብ ከዛ ደግሞ የሚቀጥለው ወር ላይ ማምረት ቀጥሎ መሸጥ ጥሩ ነው ይላሉ ወይዘሮ እመቤት። ትንሽ ሲጠነክር ደግሞ ቢዝነስ ካርድ ማዘጋጀት እሱን መስጠት፤ ሥራው ጥሩ ከሆነ ሰው ይደውላል – እንዲህ መጀመር ይችላሉ ብለዋል።

ድርጅቱ ለወደፊት ለማምረቻ እና ለማሳያ የሚሆን ቦታ በማግኘት በጣም አስፈላጊ የሆነውም የማሽን ቁጥር በመጨመር አሁን ካለበት የተሻለ ለመሆን አቅዶ እየሠራ ይገኛል።

ወ/ሮ እመቤት የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 እና የቦሌ ክ/ከተማውን አቶ ሚሊዮንን እንዲሁም ቤተሰባቸውን እና ደንበኞቻቸውን አመስግነዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …