kendi-logo

ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

ቀንዲል በአብዛኛው ሀገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም ለባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በማግኘት የተቋቋመ ነው።

ለቁም ነገር ተበደሩ፣ በጊዜው ክፈሉ፣ ዘወትር ቆጥቡ!

ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ፦ ራዕይ፣ ዓላማ፣ ተልዕኮ እና ዕሴት

ራዕይ

ብዙሀኑ ድሃ የኅ ብረተሰብ ክፍል ካለበት ስር የሰደደ ድህነት ተላቅቆ፣ በራስ የመተማመን ስሜት የሞላበት ደስተኛ ሕይወት በዘላቂነት ሲመራ ማየትና የተቋሙን ቀጣይነት ማረጋገጥ

ዓላማ

ድህነትን መቅረፍና የተቋሙን ዘላቂነት ማረጋገጥ

ተልዕኮ

በዝቅተኛና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ላልሆኑ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶች ዘመናዊ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው እንዲያድግና እንፃራዊ ለውጥ በሕይወታቸው እንዲመጣ ማድረግ፤ ከዚህም ጎን ለጎ የተቋሙን ዘላቂነት በማረጋገጥ ጠንካራ የገንዘብ ተቋም መገንባት

ዕሴት

  • ያለ አድሎኦ አገልግሎት መስጠት
  • ውጤታማነትና ምርታማነት
  • ግልጽነትና ተጠያቂነት
  • በትብብር መስራት
  • ልዩነት ማምጣት

ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የሚሠጣቸው አገልግሎቶች

የብድር ዓይነቶች

  • የቡድን ብድር፦ በጠለፋ ዋስትና የሚሰጥ ብድር
  • የግል ንግድ ብድር
  • በቤት ካርታና ፕላን፣ በሊብሬ፣ በአክስዮን ማረጋገጫ እና የደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር
  • የሠራተኞች፣ ለፍጆታ የሚውል ብድር
  • የባጃጅና መኪና መግዣ ብድር የግዢውን ግማሽ በቁጠባ በማስቀመጥ የሚሰጥ ብድር

የብድር መመለሻ ጊዜ

  • የብድር ግዜው እንደብድሩ መጠንና የደንበኛው ፍላጎት እስከ 36 ወራት የሚደርስ ይሆናል።
  • ተመጣጣኝ የወለድ ምጣኔ ያስከፍላል።
  • መደበኛ ቁጠባ
  • የግዴታ ቁጠባ
  • የሳጥን ቁጠባ
  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ
  • በጊዜ ገደብ ለሚቀመጥ ቁጠባ ላቅ ያለ ወለድ ይከፍላል
  • ከ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺሕ ብር) እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺሕ ብር) ለአንድ ዓመት ለሚያስቀምጡ እስከ 12 በመቶ የወለድ ምጣኔ ይከፍላል
  • ከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺሕ ብር) በላይ ለሆነ ቁጠባ እስከ አንድ ዓመት የሚቆይ ከሆነ እስከ 14 በመቶ የሚደርስ ወለድ ይከፍላል።
  • የነዋሪነት መታወቂያ
  • የጋብቻ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
  • የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ (TIN)
  • የዋስትና ማረጋገጫ፣ ሊብሬ፣ ካርታ፣ ፕላን
  • ፎቶ ግራፍ
  • ብድሩ የተፈለገበት ምክንያት ተገልጾ መጻፍ አለበት
  • የደረሰውን (የበሰለውን) ወለድ በየወሩ መውሰድ መቻሉ
  • የውል ጊዜ ሳይደርስ ብሩን ሊያወጡ ቢፈልጉ በመደበኛው የወለድ ምጣኔ ተሰልቶለት ብሩን ወጪ ማድረግ ማስቻሉ
  • የቁጠባ ሳጥን በአዲስ መልክ ከተለመደው የተሻለ የቁጠባ ሳጥን አዘጋጅቷል። አባላት ቤታቸው በመውሰድ መቶጠብ ይችላሉ። ማኅበሩም ባሉበት እየመጣ ያገለግላቸዋል።
  • ተቋሙ ከብድርና ቁጠባ አገልግሎት በተጓዳኝ በንግድ ሥራዎች ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።

ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ:- አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

አዲስ አበባ
  1. ጀሞ 1
  2. ሾላ ገበያ
  3. ጉርድ ሾላ
  4. ሳሪስ አቦ
  5. ሲኤምሲ ሚካኤል
ክልል ከተሞች
  1. ሻሸመኔ የተለያዩ ቅርንጫፎች
  2. ሐዋሳ አረብ ሰፈር
  3. ነገሌ አርሲ
  4. አዳማ ደራርቱ አደባባይ
  5. ቢሾፍቱ

ስልክ

  1. 011 666 80 06
  2. 011 666 80 08
  3. 0916 83 28 13
  4. 046 1105263
  5. 046 1103881
  6. 046 1101534

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.  በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …