መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የታለመ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ። ስምምነቱ የተደረገው በኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ፕሪሳይስ ኢንተርናሽናል ኮንሰልታንት እና የፈጠራ ድርጅት እንዲሁም የግሪን ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች መካከል መሆኑ ተገልጿል።

ድጋፉ በአምራች ዘርፍ ውስጥ የማያቋርጥ አፈጻጸም እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል። በገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑት በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳ እና በእጅ ሥራ የተሰማሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ አምራች ድርጅቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ የሱፍ አደምኑር ከፕሮጀክቱ ኢንተርፕራይዞች ጋር ተፈራርመዋል።
ይህ የማበረታቻ ድጋፍ በኢትዮጵያ ያሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው ተብሏል።

ድርጅቶቹ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ያደረጉት ሃብትን በመቆጠብ፣ ከአየርና ከውሃ ብክለት ነጻ በሆነ መንገድ እና ፈጠራን መሰረት ባደረገ መልኩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማምረት በመቻላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ስምምነቱን ያደረጉት በጥቃቅን እና አነስተኛ አምራች ድርጅቶች የተሰማሩ 11 ድርጅቶች እንደሆኑ የግሪን ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኽይሩ ሐሰን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ የሱፍ አደምኑር መርሃ- ግብሩ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው፣ የገንዘብ ድጋፉ ለተፈለገው ዓላማ እንዲውል ኢንተርፕራይዞቹ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።


የዜናና የምስል ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …