መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / “የከፍታ ፓኬጅ ህይወታችንን አቅልሎልናል” ገነት፣ ሰብለ እና ጓደኞቻቸው የኅትመት ሥራ
offset-printing

“የከፍታ ፓኬጅ ህይወታችንን አቅልሎልናል” ገነት፣ ሰብለ እና ጓደኞቻቸው የኅትመት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ የምሥራች ባልቻ እና አራት መሥራች አባላት በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ ኅትመት ሥራዎችን የሚሠራ እና የጽሕፈት መሣርያ (ስቴሽነሪ) እቃዎችን የሚያቀርብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • የባነር ሥራ
  • መጽሔት
  • ለተለያዩ ባልትናዎች፣ ጫማ ቤቶች እና ለሌሎችም ቢዝነሶች የቢዝነስ ካርድ ኅትመት አገልግሎት
  • የሰርግ፣ የልደት እና የሃዘን ካርዶች ማዘጋጀት
  • እንዲሁም አጠቃላይ የማስታወቂያ ሥራዎች እና
  • አጠቃላይ የጽሕፈት መሣርያ (ስቴሽነሪ) እቃዎችን የማቅረብ አገልግሎት ይሠጣል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ወ/ሮ የምሥራች ወደ ግል ሥራ ከመግባታቸው በፊት በሴክሬተሪያል ሳይንስ እና ቢዝነስ ማኔጅመንት ትምህርት ተምረው ለተወሰኑ ዓመታት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው ሰርተዋል። በዚህ ጊዜ ደግሞ አብሮ የጽሑፍ ሥራ እና አንዳንድ ከኅትመት ጋር ተያያዥ የሆኑ ሥራዎችን (ለምሳሌ እንደ ሎጎ ዲዛይን የመሳሰሉ ሥራዎች) ሲሠሩ ቆይተዋል። በሂደትም አስፈላጊውን ዕውቀት ካካበቱ በኋላ ሥራውን በግል ከቤተሰብ ጋር በመሆን ጀምረዋል። አዲስ የተጀመረው ሥራ ጥሩ ውጤት ሲያመጣ፣ ቀስ በቀስ እየሰፋ አሥር አመታትን ሲያስቆጥር፣ ወ/ሮ የምሥራች የቤተሰቡን ሥራ በመተው በራሳቸው ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ገነት፣ ሰብለ እና ጓደኞቻቸው የኅትመት ሥራ ድርጅትን መሥርተዋል።

ወ/ሮ የምሥራች ሥራውን ከብዙ ዓመት ልምድ በደንብ ስለሚያውቁት በጥሩ ሁኔታ እየሠሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ያለው የእቃ ዋጋ አለመረጋጋት በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የገለጹት፤ ለምሳሌ ጠዋት የተገዛ እቃ ከሰዓት ጨምሮ ነው የሚገኘው። ለጨረታ የተሰጠ ዋጋ ጨረታውን አሸንፈን እቃውን ለመግዛት ስንጠይቅ ዋጋው ይጨምራል። ይህ ሁኔታ ደግሞ በጣም ከባድ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ገልጸዋል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በ2merakto.com በኩል ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በተዘጋጀው የከፍታ ፓኬጅ በኩል በተዘጋጀው የገበያ ትስስር ፓኬጅ ማስታወቂያ እያዩ በሚደውሉ ሰዎች እና ወ/ሮ የምሥራች ራሳቸው በፊት የሚሠሩበት ቤት የሚመጡ ሥራዎችን በመውሰድ እና በሰው በሰው ትውውቅ ነው። ይሁና እና ድርጅቱ በሙሉ አቅሙ ሥራ መሥራት የጀመረው በቅርብ ነው። በተለያዩ ምክንያቶች በደንብ መሥራት እንዳለበት መሥራት አልቻለም፤ አሁን ግን የከፍታን ፓኬጅ በመጠቀም የማስታወቂያ እና የጨረታ አገልግሎት በደንብ እየተጠቀመ ይገኛል።

ድርጅቱ ሲመሠረት የነበረው መነሻ ካፒታል አርባ ሺህ ብር ሲሆን አሁን ካፒታሉ መቶ ሺህ ብር ደርሷል። ይህ ድርጅት በአንድ ቀን እስከ ሃምሳ ሺህ የሚደርስ የወረቀት ሥራ ተቀብሎ የመሥራት አቅም አለው። በተጨማሪም የባነር ሥራዎችን ደግሞ በቀን እስከ አምስት መቶ ካሬ ድረስ የሚደርስ የባነር ሥራ የመሥራት አቅም አለው። ለአምስት ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ተፅዕኖ በጣም ከባድ ነበር ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ለሁለት ወር ገደማ ሥራ አቁሞ ነበር። ከሁለት ወር በኋላ ሰዉም ሲረጋጋ ቀስ በቀስ ወደ ሥራ ገብቷል። ድርጅቱ ወደ ሥራ ቢገባም ትዕዛዝ ይዞ የሚመጣ ደንበኛ ቁጥር ግን አሁንም ድረስ እንደ ቀነሰ ነው።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ ወደ ፊት እሁን ያለው የእቃ ዋጋ ገበያ ከተረጋጋ፣ የጽዳት እቃዎች ፈቃድ በማውጣት በጽዳት እቃዎች ሥራ ለመሰማራት በእቅድ ላይ ይገኛል። እንዲሁም ድርጅቱ በውስጡ ያለውን የተማረ የሰው ኅይል ለማጠናከር በሦስት ዓመታት ውስጥ የተሻለ የሰው ኅይል እንደኖረው አቅዶ እየሠራ ይገኛል። ይህንንም ለማሳካት ሁሉም የድርጅቱ አባላት ብርሃን እና ሰላም የኅትመት ኮሌጅ እየተማሩ ይገኛሉ።

“አንድ ቢዝነስ ያለው ሰው ስነምግባር ያለው፣ ታጋሽ እና ጠንቃቃ ሊሆን ይገባል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተለዩ ወጣ ያሉ ሥራዎች ሲመጡ ኪሳራ እንዳላቸው አውቆ የሚገባበት ሥራ አለ፤ ይህም ማለት ሥራውን ብሠራው ከማገኘው ጥቅም አንጻር ኪሳራው አይጎዳኝም ተብሎ የሚገባ ሥራ አለ። እነዚህን ሥራዎች ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ እነዚህን ነገሮች ለማወቅ ደግሞ ልምድ በጣም አስፈላጊ ነው። አሁን ያለው የገበያ ሁኔታ ራሱ ትዕግስት የሚጠይቅ ነው” ሲሉ ወ/ሮ የምሥራች ገልጸዋል።

ወ/ሮ የምሥራች ስለ ከፍታ አገልግሎት የሚከተለውን ብለዋል “በጣም ጠቅሞናል በአገልግሎቱ ላይ የሚገኙት የጨረታ ማስታወቂያዎች የተሟሉ ናቸው። በፊት ትልቁ ችግር የነበረው ጋዜጣ መፈለግ እና ጨረታውን ማግኘት ነበር።” ለዚህም እሳቸው (ወ/ሮ የምሥራች) ኢንተርኔት ላይ ይፈልጉ ነበር፤ በተጨማሪም ሁሉንም ጨረታዎች የሚይዝ ጋዜጣ ወይም መጽሔት የት ነው ማገኘው ብለው ይቸገሩ ነበር። ጋዜጣ አዟሪዎችን በቋሚነት ለመቅጠር ሃሳቡ ራሱ ነበራቸው። ወ/ሮ የምሥራች አሁን ግን የከፍታ አገልግሎት ሁሉንም ጨረታ እንደሚፈልጉት አድርጎ ስላመጣላቸው በጣም ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …