መነሻ / የቢዝነስ ዜና / በኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና 13,838 ብር ተሸጠ

በኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና 13,838 ብር ተሸጠ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ በቆየው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ አንድ ኪሎ ግራም ቡና በ13ሺህ 838 ብር መሸጡን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በውድድሩ ያሸነፈው ቡና አንድ ኪሎ በ407 የአሜሪካን ዶላር ወይም በ13 ሺህ 838 ብር መሸጡን ተናግረዋል። ጨረታውን ያሸነፈው ‘ማሩያማ’ የተባለ የጃፓን ኩባንያ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አሸናፊው በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ያሉት አርሶ አደር ንጉሴ ገመዳ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጨረታው የተካሄደባቸው 28 ቡናዎች ደግሞ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን 348 ሺህ 690 ዶላር የተሸጡ ሲሆን ይህም በ ‘ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ’ የቡና ጨረታ ውድድር ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡን ጠቁመዋል።

“ውድድሩ ኢትዮጵያ የተለያየ የቡና ዝርያ ያላት አገር መሆኗን ለዓለም ለማሳየት መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል”  ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ከዚያም ባለፈ  ከ33 አገሮች የተውጣጡ 168 ቡና ገዢዎች አንደኛ የወጣውን ቡና ለመጫረት ፍላጎት ማሳየታቸውን አንስተዋል።


የዜናው ምንጭ፡- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …