መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ዮናታን ታደሰ እና ሦስት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት እና የማስታወቂያ ሥራዎች፣ የባነሮች፣ የመጽሐፎች እና አጠቃላይ የኅትመት ሥራ የሚሠራ ድርጅት ነው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ዮናታን ይህን ድርጅት ከመመሥረታቸው በፊት የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ በኅትመት ሥራ የመሥራት እድሉን አገኙ። በዚህም ሥራ ለስምንት ዓመት ተቀጥረው በመሥራት አሳልፈዋል። ከስምንት ዓመት ቆይታ በኋላ በዘርፉ ያለው ሰፊ የሥራ ዕድል በመገንዘብ ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ሀሌታው ሀ የኅትመት እና ማስታወቂያ ድርጅት መሠረቱ። ።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው ጨረታን ብቻ በመከታተል ሲሆን ይህንንም ያደርግ የነበረው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በመከታተል ነበር። አሁን ግን 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም በመላው ኢትዮጵያ ላይ የሚወጡ የጨረታ መረጃዎችን በማግኘት የሥራ ዕድሉን ማስፋት ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በዚሁ በጨረታ አሸንፎ በጥሩ ሁኔታ ሥራውን አጠናቅቆ ካስረከባቸው ደንበኞች ጋር በሚፈጠሩ ስምምንነቶች እና ውሎች ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ ሲመሠረት የነበረው ሦስት መሥራች አባላት እና መነሻ ካፒታሉ ደግሞ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ብር ነበር ። አሁን ላይ የካፒታል አቅሙን ወደ ሁለት ሚሊዮን ብር ማሳደግ የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለስምንት ቋሚ እና ለአራት ጊዜያዊ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ድርጅት መሆን ችሏል።

ድርጅቱ ከተመሠረተ ወደ ተሻለ መንገድ ሊራመድ የቻለው ዋናው የመሥሪያ ቦታ ምቹ ማድረግ መቻሉ እና ቴክኖሎጂ በጣም መጠቀሙ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ገልጸዋል። በዚህም ወደ ሰባ የሚጠጉ ሥራዎችን በክልልም በአዲስ አበባ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከዐሥር ድርጅቶች ጋር በኮንትራት እየሠራ ይገኛል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ ጥሩ እድል በመቀየር ለተለያዩ ድርጅቶች የፊት ማስክ ኅትመት ሥራ በመሥራት ጠቀም ያለ ትርፍ ሊያገኝ ችሏል።

ምክር

አንደ አቶ ዮናታን ገለጻ ቢዝነስ ያለው ሰው ቢዝነሱ እንዲያድግ ከፈለገ የደንበኛ ፍላጎትን መጠበቅ ምንጊዜም ቀዳሚ ሥራ መሆን አለበት፤ ይህ ከሆነ ምንም ዐይነት ቢዝነስ ማደግ እና መሥፋት እንደሚችል ገፀዋል። ወደ ኅትመት ሥራ የሚገቡ ሠዎች ደግሞ ዘርፉ ሰፊ እድል ቢኖረውም ትዕግስት ይጠይቃል። ይህ ማለት ብዙ ሥራ የሚሠራው በጨረታ በመሆኑ ምርት በተባለው ጊዜ መድረስ አለበት። ይህን ለማድረግ ደግሞ እቃ ከሌለ ዋጋ ይወደዳል ይህ ደግሞ ሥራን ያጓትታል ወይም በኪሣራ የሚሠራበት እጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ተረድተውና ተዘጋጅተው ወደ ሥራው ቢገቡ መልካም ነው ሲሉ ይመክራሉ።

እቅድ

ድርጅቱ ከአምስት አመት በኋላ የሚሠራውን ሥራ በማስፋት ትልቅ ድርጅት የመሆን እቅድ አለው።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …