መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ጠልሰም ኅትመት እና ማስታወቂያ

ጠልሰም ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ አንጋት ገብረ ጊዮርጊስ በ2013 ዓ.ም. ነው። ጠልሰም አጠቃላይ የኅትመት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ የሚሠራቸው የኅትመት ሥራዎች

  • ማግ (ኩባያ) ላይ ኅትመት
  • የትራስ ኅትመት
  • ሾፒንግ ባግ ኅትመት
  • ሻማ ኅትመት
  • እምነበረድ ኅትመት
  • ቲሸርት ኅትመት
  • መሐፍ ኅትመት
  • ማስታወሻ ደብተሮች ኅትመት
  • እስክሪብቶ ኅትመት
  • ፖስት ካርድ ኅትመት
  • የህጻናት ኮዳ ኅትመት
  • እንቆቅልሽ (Puzzle) ኅትመት
  • ሰርተፍኬት ኅትመት
  • የቁልፍ መያዣ ኅትመት
  • ባነር እና ስቲከር እና ሌሎችም

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ወ/ሮ አንጋት ወደ ኅትመት ሥራ ከመግባታቸው በፊት በመንግሥት ሥራ ውስጥ በአስተማሪነት ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ባለቤታቸው በነበራቸው የኢንተርየር ዲዛይን ዕውቅት እይሠሩ ስለነበር ከባለቤታቸው ጋር ለተወሰነ ጊዜ እየተማሩ ሠርተዋል። ከኢንቲርየር ዲዛይን ሥራ ጋር ይመጡ የነበሩ ሥራዎች ከግራፊክስ ሥራ ጋር ተያያዥነት ስለነበራቸው፣ የኅትመት ሥራ ዕውቀቱ ካለ በትንሽ ካፒታል መሠራት የሚቻል ሥራ  መሆኑን እና ሥራው ትጋት ካለ የሚቆም ሥራ እዳልሆነ ከተረዱ በኋላ ወ/ሮ አንጋት የግራፊክስ ሥልጠና ወስድዋል። ሥልጠናውን እንደጨረሱ የተወሰነ ገንዘብ ቆጥበው ስለነበር አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ፕሪንተር በመግዛት ወደ ኅትመት ሥራ ተቀላቅለዋል።

ድርጅቱ ከተመሠረተ በኋላ ወደ ሲስተም መግባት በጣም አስቸጋሪ ነበር። ተስፋ ሳይቆርጡ እንዲቀጥሉ ያደረጋቸው አንደኛው ምክንያት ስለሥራው የነበራቸው ዕውቀት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ሥራውን ለመሥራት የተጠቀሟቸው የተለያዩ መንገዶች ናቸው። ከተጠቀሟቸው መንገዶች ውስጥ ሥራዎችን አውትሶርስ ማድረግ፤ ለምሳሌ፦ የስቲከር ሥራዎችን በራሳቸው እና በሌሎች በማሠራት እንዲሁም ትልቅ ሥራዎችን ከሌሎች በመቀበል በመሥራት እና ለሌሎች በመስጠት። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የ2merkato.com አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ሲሆን በዚህም ዐምስት ጨረታዎችን ማሸነፍ ችለዋል። እንዲሁም የኅትመት ሥራ ያስፈልጋቸዋል ብለው የሚያስቧቸውን ቢዝነሶች የ2merkato.com B2B ፕላትፎርም በሆነው ቢዝነስ ዲሬክተሪ ላይ በመግባት እና በመደወል ሥራዎችን ሠርተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በሰው በሰው የሚመጡ ሥራዎች ሠርተዋል። ድርጅቱ አሁን ለሦስት ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። እንዲሁም ደግሞ ሥራዎችን የመሥራት ዐቅሙ በጥራት እና በብዛት ጨምሯል። ድርጅቱ የኅትመት ሥራዎችን ከሠራላቸው ድርጅቶች መካከል ኤልፎራ፣ አረቄ ፋብሪካ፣ እና የጥበቃ ሥራ ለሚሠሩ ኤጀንሲዎች የሚጠቀሱ ሲሆኑ፤ እንዲሁም የተለያዩ የኅትመት ሥራዎችን ለጤና ጣቢያዎች እና ወረዳዎች እየሠራ ይገኛል።

ድርጅቱ ሥራዎችን ከመፈለግ በተጨማሪ ደግሞ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም ሥራዎችን እንዲመጡለት ያደርጋል። በዚህም የ2merkato.com B2B ፕላትፎርም በሆነው ቢዝነስ ዲሬክተሪ ላይ በማስተዋወቅ እንዲሁም ከሶሻል ሚዲያ ድግሞ ፌስቡክ ላይ እየተጠቀመ ይገኛል። ኅትመት ሥራ ላይ ቴክኖሎጂ መጠቀም ምንም ጥያቄ የለውም፤ ሶሻል ሚዲያ በጣም ወሳኝ እና ጠቃሚ ሥራዎችን ያገናኛል ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ጠቅሰዋል።

ኅትመት ሥራ ላይ አሁን ያለው ተጠቃሽ ችግር ወረቀት አስመጪ ድርጅቶች ወረቀቱን አስመጥተው ራሳቸው እንደገና ጨረታ ላይ የሚሳተፉበት ሁኔታ ከባድ ነው። በተለይ ደግሞ ትንሽ ወይም አነስተኛ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሰዎች በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ድርጅቱ በኮቪድ ጊዜ ከባድ ሁኔታዎችን በማሳለፉ ተዘግቶ ነበር። ሥራ ቀንሶ ሙሉ በሙሉ ቆሞ ነበር የሚቻል ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ብዙ ሥራዎች ተበላሽተዋል፤ ጊዜውን ለማለፍ ጥቂት ማሽኖችም ለመሸጥ ተገዶ ነበር። የኮቪድ ፍራቻ በሂደት ሲቀንስ ድርጅቱም ብድር በመበደር እንደ አዲስ ሥራውን ጀምሯል።

ምክር እና ዕቅድ

ቢዝነስ ላይ መታወቅ አለበት የሚባለው ነገር ምንድ ነው? ሂሳብ አያያዝ፤ አንድ ሰው ወጪ እና ገቢ መለየት አለበት። ይህ በጣም ጠቃሚ ነው ሁሌም ትርፍ አይኖርም ኪሣራም ሊኖር ስለሚችል ይህንን ማወቅ አለበት። ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ጋር ያለው ነገር መስተካከል በጣም አስፈላጊ ነው። ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ጋር ምን ያስፈልጋል የሚለውን መታወቅ አለበት፤ መሟላት ያለባቸው ነገሮችን አሟልተው ወደ ሥራ ቢገቡ ጥሩ ነው።

የኅትመት ሥራ ለማደግ ዋናው ነገር ደንበኛን ማክበር ሲሆን፤ ይህ ማለት ደግሞ የወሰዱትን ሥራ በተባለው ጊዜ በጥራት ሠርቶ ማስረከብ ከተቻለ ደግሞ ቀድሞ መጨረስ ለኅትመት ሥራ እድገት በጣም አስፈላጊ ነው። አሁን ያለው የዋጋ አለመረጋጋት አስቸጋሪ ነው፤ ስለዚህ ይህን ታሳቢ በማድረግ ከደንበኛ ጋር ተነጋግሮ ሥራን መጀምር አለመግባባትን ስለሚያስቀር ዘላቂነት ያለው ግንኙነት እንዲፈጠር ያስችላል።

የግል ሥራ ላይ ከባድ ኅላፊነቶች እንዳሉ ሁሉ፤ ደስ የሚል ነገርም አለው። ይህም ባለቤቱ ራሱ ስለሆነ የተሻለ ነገር ለመፍጠር ካሰበ ማድረግ ይችላል። እንዲሁም ትዕግስት እንዲኖር ያደርጋል። ይህም በፊት እኔ ይህንንማ አላደርግም የሚለውን ነገር ለራሱ ስለሆነ እራሱ በመታገስ እና በመሞከር ለውጥ ማምጣት እንዲችል ይሆናል።

ድርጅቱ ወደ ፊት ትልቅ የታወቀ ማተሚያ ቤት የመሆን ዕቅድ አለው።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …