ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ1993 ዓ.ም ተመሥርቶ በብድር እና ቁጠባ ዘርፍ እየሠራ ያለ ማኅበር ነው። ከ24,000 በላይ አባላት እና ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ሀብት አለው። በቦሌ ደምበል (ኦሎምፒያ) አካባቢ በ1083 ካሬ ሜትር ላይ ባለ 4 ፎቅ ሕንጻ እና ለቢሮ ምቹ የሆኑ ተጨማሪ ክፍሎች ያሉት ግቢ ባለቤትም ነው። በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በ6 ቅርንጫፎች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።
ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶች
ራዕይ
የማህበሩን አባላት በኑሮአቸው፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ መስክ ተሻሽለው በክብርና በብልጽግና ህይወትን ሲኖሩ ማየት ነው።ተልዕኮ
የማበሩን አባላት በተመጣጠነ ዋጋ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን በማጎልበት የተሻለ አማራጭ አድል መፍጠርዕሴቶች
- ጥራት እና ልቀት ያለው አገልግሎት
- ፈጠራን የሚያበረታታ
- ከአድልዖ የፀዳ
- ተአማኒ የሆነ
- ብቃት
- አጋርነት
- ተጠያቂነት
- ግልጽነት
- ሩህሩህነት
ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
በማኅበሩ የቁጠባ አገልግሎቶች ከተመጣጣኝ የቁጠባ ወለድ 7% እና በድርድር የሚወሰን የጊዜ ገደብ ቁጠባ ወለድ ክፍያ ጋር
የውዴታ ግዴታ ቁጠባ
- ማንኛውም የማኅበሩ አባል በየወሩ በመደበኛነት የሚቆጠብ ቁጠባ
በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ቁጠባ
- አባላት በማንኛውም ጊዜ ወጪ ሊያደርጉ የሚችሉ ቁጠባ/ የባንክ ዓይነት አገልግሎት
የፕሮቪደንት ፈንድ ቁጠባ
- ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የፕሮቪደንት ፈንድ በተመጣጣኝ ወለድ ማስቀመጥ
ለህጻናት የሚቀመጥ የረጅም ጊዜ ቁጠባ
- ማኅበሩ ለህጻናትና ወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል
የቁጠባ ሣጥን ቁጠባ
- ለአነስተኛ ቁጠባ በቤታቸው ቆጥበው ተጠራቅሞ ሂሳባቸው እንዲገባ የሚደረግ የቁጠባ ዓይነት ነው።
የኢንቨስትመንት ብድር
ለንግድ ዘርፍ ማቋቋሚያ ወይም ማስፋፊያ፣ ለቤት ግንባታ ሥራ ወይም እድሳት የሚውል፣ ለቋሚ ንብረት ግዢ (ለመኪና፣ ለቤት፣ ለመሬት ሊዝ ክፍያ) ለከፍተኛ ትምህርት ክፍያ፣ ሌሎች ከኢንቨስትመንት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ሁኔታዎ፦ የብድሩ መጠን እሰከ 3 ሚሊዮን ብር ድረስየማኅበራዊ ጉዳይ ብድር
ለሰርግ፣ ለቀብር እና ለሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች፦ የብድሩ መጠን እስከ 100 ሺህ ብር ድረስልዩ ብድር
ለሕክምና እና ለልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ብድርበፕሮጀክት ላይ የተመሠረተ ብድር
የዚህ ይብድር ዓይነት፦ የብድር ጣሪያው እስከ ብር 3,000,000.00 ይደርሳል- በቁጠባና በዕጣ ዋስትና
- በደመወዝ ዋስትና
- በቋሚ ንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
- የመኪና ዋስትና
- የኮንስትራክሽንንና ሌሎች ማሽነሪዎች ዋስትና
- በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ነዋሩ የሆነና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
- ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሠርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
- በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመርያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ/ነች
- በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው
አንድ አመልካች አባል አንዲሆን ሲፈቀድለት
- የመመዝገቢያ ብር 1000
- የቁጠባ መክፈቻ ብር 500
- ለሼር ብር 1000 በድምሩ 2500 ብር እና
- ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍና የቀበሌ መታወቂያ / የታደሰ ፓስፖርትን መንጃ ፍቃድ
- ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም!
- የአንድ ዕጣ ዋጋ 1000.00 ብር ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛ የዕጣ መጠን አንድ ነው።
- አንድ አባል በጠቅላላ ጉባሌ ተወካይ አባላት አንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
- በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የዕጣ እና ቁጠባ ምጥጥን መሠረት አንድ አባል በየጊዜው 1፡3.5 ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።
ጆሽዋ ቁጠባና ብድር አድራሻ
ዋና መሥሪያ ቤት፦ ኦሎምፒያ ኤቢሲ ትሬዲንግ አጠገብ 40 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፦- +251 115 58 44 14
- +251 115 58 44 15
- +251 115 58 44 16
- +251 115 58 44 18
- +251 115 58 29 70
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ፒያሳ ቅርንጫፍ | ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ሀሮን ታወር / ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት | +251 993 53 15 30 +251 930 05 06 87 |
ጎተራ ቅርንጫፍ | ጎተራ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት፣ ንግድ ባንክ ያለበት ሕንጻ ላይ አንደኛ ፎቅ | +251 114 70 72 11 +251 144 70 21 99 |
ዋና መሥርያ ቤት | ኦሎምፒያ፣ ኤቢሲ ትሬዲንግ አጠገብ 40 ሜትር ገባ ብሎ | +251 115 58 44 14 +251 115 58 44 15 +251 115 58 44 16 +251 115 58 44 18 +251 115 58 29 70 |
አየር ጤና ቅርንጫፍ | አየር ጤና፣ ሳሚ ካፌ ጎን ህብረት ባንክ ሕንጻ | +251 113 69 41 97 +251 113 69 39 78 |
መገናኛ ቅርንጫፍ | ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ላይ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ታላቁ ተልዕኮ ሕንጻ ላይ | +251 116 66 11 02 +251 116 66 09 87 |
ልደታ ቅርንጫፍ | ልደታ ቤተክርስትያን ፊት ለፊት አዋሽ ባንክ ሕንጻ ላይ | +251 115 57 38 91 +251 115 57 40 92 |
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ጆሽዋ ሁለገብ ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።