መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2 ቢሊየን ብር ለጥቃቅን እና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት አድርሻለሁ አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2 ቢሊየን ብር ለጥቃቅን እና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት አድርሻለሁ አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በልማት ባንክ በኩል 2 ቢሊየን ብር ለጥቃቅንና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት እንዲደርስ ማድረጉን ገለጸ።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ፍቃዱ ደግፌ እንደገለጹት፣ መንግስት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እያከናወነ ካለው ማኅበራዊ የጤና ክንውን ባሻገር በጥቃቅን እና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ላይ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ለመቀነስ እየሠራ ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ በልማት ባንክ በኩል 2 ቢሊየን ብር ለጥቃቅን እና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት እንዲደርስ መደረጉን አስረድተዋል።

እርምጃው መንግስት የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅ እና የፋይናንስ ዘርፉን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለመታደግ እየሠራ እንዳለ ማሳያ ነው ብለዋል – ምክትል ገዥው። በተጨማሪም በዚህ ዘርፍ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ ከፍል ሊል እንደሚገባ አሳስበዋል።


ምንጭ፡- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

ይህንንም ይመልከቱ

TUC_NSP_2merkato_poster_ad_20221031-04

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ …