መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት ሁሉንም የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶችና ወጣቶች ለማገልገል የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ባሁኑ ወቅት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጠቅላላው 29 ቅርንጫፎችና 4 ንዑስ ቅርንጫፎች ያሉት ተቋም ነው። ተቋሙ የኅብረተ ሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ህይወት ለመለወጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ማኅበሩ ላለፉት ዐሥራ ስምንት ዓመታት ደንበኞቹን በማገልገል ላይ ይገኛል ወደፊትም አገልግሎቱን በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ለማስፋፋት አቅዶ እየሠራ ይገኛል።
- የእርሻ ብድር፦ ለእርሻ ሥራ የሚውል ደንበኞች በቡድን ወይም በግል የሚወስዱት የብድር አይነት ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ብድሩ ይመለሳል።
- ጥቃቅን የሴቶች ብድር፦ ሴቶች በቡድን ተደራጅተው ለጥቃቅን ንግድ ሥራዎች የሚወስዱት የብድር ዓይነት ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ብድሩ ይመለሳል።
- የሠራተኞች ብድር፦ ለመንግሥትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የከፈላል።
- የሴቶች ብድር፦ ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች በንብረት ዋስትና በተመጣጣኝ ወለድ ከ1-3 ዓመት ድረስ የሚቆይ እስከ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ድረስ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
- ለግለሰብ የሚሰጥ ብድር፦ በንብረት ዋስትና ለንግድ ሥራ በግል ከ1-4 ዓመት ድረስ የሚቆይ እስከ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ድረስ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
- ዋሽ ብድር፦ የውሃ መስመር ለማስገባት፣ መጸዳጃ ቤት ለማሠራት፣ የውሃ ማጣሪያና ማጠራቀሚያ ለመግዛት የሚውል የብድር ዓይነት ነው።
- ሶላር ብድር፦ በፀሓይ ኃይል የሚሠሩ የኃይል ምንጭ ምርቶችን ለመግዛት የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
በደሞዝ ብድር ለመውሰድ የሚያስችል መጠን | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
ቁጥር | ደሞዝ | የሚችለው ብር | ቁጠባ (10%) | ያገልግሎት ክፍያ (4%) | የደብተር | ድምር |
1 | 5,000-5,500 | 40,000 | 4000 | 1600 | 40 | 5,640 |
2 | 6,000 | 50,000 | 5000 | 2000 | 40 | 7040 |
3 | 7,000 | 55,000 | 5500 | 2200 | 40 | 7740 |
4 | 8,000 | 65,000 | 6500 | 2600 | 40 | 9140 |
5 | 9,000 | 75,000 | 7500 | 3000 | 40 | 10540 |
6 | 10,000 | 80,000 | 8000 | 3200 | 40 | 11240 |
7 | 11,000 | 90,000 | 9000 | 3600 | 40 | 12640 |
8 | 12,000 | 100,000 | 10000 | 4000 | 40 | 14040 |
9 | 13,000 | 110,000 | 11000 | 4400 | 40 | 15440 |
10 | 14,000 | 115,000 | 11500 | 4600 | 40 | 16140 |
11 | 15,000 | 125,000 | 12500 | 5000 | 40 | 17540 |
12 | 16,000 | 135,000 | 13500 | 5400 | 40 | 18940 |
13 | 17,000 | 140,000 | 14000 | 5600 | 40 | 19640 |
14 | 18,000 Above | 150,000 | 15000 | 6000 | 40 | 21040 |
- የደብተር ቁጠባ፦ ተበዳሪ የሆኑና ያልሆኑ ደንበኞች በተሻለ ወለድ በማንኛውም ወቅት ገንዘባቸውን በማስቀመጥ በፈለጉት ጊዜ ወጪ የሚያደርጉት የቁጠባ ዓይነት ነው።
- የሳጥን ቁጠባ፦ የድርጅቱን የቁጠባ ሳጥን በነጻ በመውሰድ የሚቆጥቡበትና ውድ ጊዜአቸውን ሳያባክኑ ባሉበት ቦታ የድርጅቱ ሠራተኞች በመገኘት በተቀመጠው መመርያ መሰረት በሕጋዊ ደረሰኝ ገንዘቡን የሚቀበሉበት የቁጠባ ዓይነት ነው።
- የተቋማት ቁጠባ፦ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው የግልና የሕዝብ ተቋማት፤ ማኅበራትና ድርጅቶች የሚቆጥቡት የቁጠባ ዓይነት ነው።
- መተማመን (ልዩ) ቁጠባ፦ ይህ የቁጠባ ዓይነት በማንኛውም ጊዜ ወጪ አድርገው ሊጠቀሙበት የሚችሉት የገንዘብ መጠን የሚፈቅድ ከመሆኑም በላይ እንደሚቀመጥበት ጊዜ ብዛት በስምምነቱ መሠረት ከመደበኛው ቁጠባ የተሻለ ወለድ ያስገኛል።
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ፦ በጊዜ የተገደበ ቁጠባ ሆኖ እንደ ገንዘቡ መጠንና እንደሚቆይበት ጊዜ የወለዱ መጠን ለድርድር ክፍት የሆነና ንግድ ባንኮች ከሚሰጡት የቁጠባ ወለድ በላይ የሚገኝበት የቁጠባ ዓይነት ነው።
- የህጻናት ቁጠባ፦ ልጆችና ወላጆች የቁጠባ ባህል እንዲያዳብሩና ወደፊት ለልጆች ከፍተኛ ትምህርት ወይም የራሳቸውን ሥራ መሥራት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት በወላጆች ፈቃድ የሚንቀሳቀስ የቁጠባ ዓይነት ሲሆን እንደ ቆይታ ጊዜው የወለድ መጠኑ ዳጎስ ያለና እየጨመረ የሚሄድ ይሆናል።
- እድሜዎ ከ 18 እስከ 60 አመት ከሆነ
- በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ከስድስት ወር በላይ ከቆዩ
- የታደሰ ስድስት ወር ያላለፈው ንግድ ፍቃድ ካለዎ
- ለማስያዣ ቤት፣ ተንቀሳቃሽ መኪና፣ ዋስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለብዎት
- በሚኖሩበት ቀበሌ ከአንድ ዓመት ባላይ መቆየትዎን የሚመሰክር የታደሰ መታወቂያ
ቅርንጫፍ | ስልክ ቁጥር |
---|---|
ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ወሎ ሰፈር | 0113 69 87 12፣ 0113 69 82 52፣ 0114 70 68 67 |
ቦሌ ቅርንጫፍ | 0118 29 85 11 |
መካኒሳ ቅርንጫፍ | 0113 69 87 39 |
ጉለሌ ቅርንጫፍ | 0111 54 66 32 |
አዲስ ከተማ | 0112 73 53 66 |
የካ | 0116 68 73 80 |
ሞጆ ቅርንጫፍ | 0222 36 34 40 |
አርሲ ሮቤ ቅርንጫፍ | 0224 43 03 09 |
አርሲ ነጌሌ ቅርንጫፍ | 0461 16 20 08 |
አሰላ ቅርንጫፍ | 0223 31 57 91 |
ዝዋይ ቅርንጫፍ | 0464 41 22 60 |
ደንቢ ዶሎ ቅርንጫፍ | 0575 55 19 31 |
ሁሩታ ቅርንጫፍ | 0223 34 00 36 |
መቂ ቅርንጫፍ | 0228 18 05 34 |
አዳማ ቅርንጫፍ | 0221 12 98 72 |
ሻሸመኔ ቅርንጫፍ | 0462 11 50 07 |
ወልቂጤ ቅርንጫፍ | 0118 30 60 23 |
ወሊሶ ቅርንጫፍ | 0118 81 31 13 |
ኢቴያ ቅርንጫፍ | 0223 35 03 81 |
ኦጎልቾ ቅርንጫፍ | 0224 75 02 42 |
ወላይታ ቅርንጫፍ | 0461 80 40 88 |
እምድብር ቅርንጫፍ | 0113 31 08 11 |
አለም ጤና ቅርንጫፍ | 0221 150381 |
ሆሳዕና ቅርንጫፍ | 0468 55 91 86 |
ቦዲቲ ቅርንጫፍ | 0468 95 81 83 |
ስሬ ቅርንጫፍ | 0223 30 06 66 |
ሳጉሬ ቅርንጫፍ | 0223 381695 |
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።