መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ምሳሌ የብድር አገልግሎት – ከዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ.

ምሳሌ የብድር አገልግሎት – ከዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ.

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. የኅብረተ ሰቡን ፍላጎት ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በየጊዜው አሠራሩን በቴክኖሎጂ እያዘመነ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱን ለበርካታ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ቅርንጫፎችን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ወጣቱን የኅብረተ ሰብ ክፍል ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ምሳሌ የተባለ የብድር አገልግሎት አዘጋጅቷል።

ምሳሌ የብድር አገልግሎት መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ የንግድ ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ እና ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በቡድን እና በተናጠል የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ በተቋሙ የተዘጋጀ የብድር ዓይነት ነው። የብድር አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስፈልጉ ዋና ዋና መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
  • በፈቃደኝነት በቡድን ለመደራጀት እና በእርስ በእርስ ዋስትና ለመበደር ፍላጎት ያላቸው መሆን፤
  • በቡድን የሚደራጁ ወጣቶች ብዛት ከ3 እስከ 5 ይሆናል፤
  • የእያዳንዱ ቡድን አባል እርስ በእርስ በሚገባ መተዋወቅና መግባባት አለባቸው፤
  • ሁሉም የቡድኑ አባላት ብድሩ ተመላሽ አንዲሆን በጋራ መሥራት እና ኃላፊነት መውሰድ (አንድ የቡድን አባል ብድሩን መክፈል ባይችል ሌሎች የቡድኑ አባላት ለመክፈል እንደሚገደዱ በሚገባ መገንዘብ አለባቸው)፤
  • የቡድን አደረጃጀቱ ከቤተሰብ አባላት የተውጣጣ ሊሆን አይችልም (የቤተሰብ ሲባል የቅርብ ዝምድና ያላቸው የቤተሰብ አባላት እና በአንድ የገቢ ምንጭ የሚተዳደሩ የቤተሰብ አባላትን ያካትታል)፤
  • የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አድሜያቸው ከ18 እስከ 40 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ሊሆኑ ይገባል፤
  • የአመልካቾች የሥራ ቦታ ተቋሙ በሚገኝበት የሥራ አካባቢ መሆን አለበት፤
  • አመልካቾች የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • አመልካቾች የብድሩን 10% ቅድመ ብድር ቁጠባ መቆጠብ አለባቸው (ደንበኞች ቅደመ ብድር ቁጠባን ከብድሩ ላይ እንዲታሰብ ማድረግ ይችላሉ)፤
  • የብድር አመልካቾች ብድሩን ለመመለስ በሚያስችል የንግድ ሥራ ላይ መሠማራት ይኖርባቸዋል፤
  • አመልካቾች ከየትኛውም አበዳሪ ተቋም ተበድረው ተመላሽ ያላደረጉት ብድር ሊኖር አይገባም፤
  • አመልካቾች የወሰዱትን ብድር ለመክፈል የሚያስችል መደበኛ ገቢ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፤
  • ሁሉም አመልካቾች በተቋሙ መመሪያ መሠረት ለመተዳደር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
አመልካቾች ለሚበደሩት ብድር ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማስያዣነት መጠቀም ይችላሉ።
  • የቡድን ዋስትና
  • የቁጠባ ዋስትና
  • የቋሚ ተቀጣሪ ሠራተኛ የደሞዝ ዋስትና ወይንም የንብረት ዋስትና
አመልካቾች መጠየቅ የሚችሉት ከፍተኛ የብድር መጠን እንደ ሥራው አይነትና በገቢ መጠን የሚወሰን ይሆናል።
የብድር ዓይነትበ1ኛ ዙር የሚሰጠው ከፍተኛ የብድር መጠን በብርበ2ኛ ዙር የሚሰጠው ከፍተኛ የብድር መጠን በብርበ3ኛ ዙር የሚሰጠው ከፍተኛ የብድር መጠን በብርበ4ኛ ዙር የሚሰጠው ከፍተኛ የብድር መጠን በብር
በቡድን ዋስትና የሚሰጥ ብድር20,00030,00040,00050,000
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር50,00050,00050,00050,000
የግለሰብ ብድር50,00050,00050,00050,000
ተበዳሪዎች የወሰዱትን ብድር የሚመልሱበትን ጊዜ መነሻ በማድረግ የአጭር፤ የመካከለኛ ወይም የረጅም ጊዜ ብድር ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜም ከ 3 ወራት - 24 ወራት ሊራዘም ይችላል።
ደንበኞች ከተቋሙ ብድር ሲወስዱ የሚከፍሉት የወለድ እና የአገልግሎት ክፍያዎች
ተ.ቁየብድር መመለሻ ጊዜዓመታዊ ወለድወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያየምዝገባ ክፍያየኢንሹራንስ ክፍያየምዝገባ ክፍያ
1እስከ 2 ዓመት21%100 ብር100 ብር2%30 ብር

ስለዳይናሚክ የበለጠ ለመረዳት እና ስልክ ቁጥሮችን ለማግኘት ይሄን ገጽ ይመልከቱ። 

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …