መነሻ / የቢዝነስ ዜና / ተቋርጦ የከረመው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ

ተቋርጦ የከረመው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ

በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ዝግ ሆኖ የቆየው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ።

የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግሥት የመደበኛና የሞባይል ኢንትርኔት አገልግሎቶችን በመላዋ አገሪቱ እንዲቋረጥ አድርጎ መቆየቱ ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የዋይ-ፋይ የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱ ይታወቃል። በርካታ ተጠቃሚ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ደግሞ ዛሬ ሐሙስ በበርካታ ስፍራዎች ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ከአዲስ አበባ ባሻገር በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችም የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ደውዬ አጣርቼያለሁ ሲል የዘገበው ቢቢሲ፣ አገልግሎቱ የተመለሰው በመላ አገሪቱ ይሁን አይሁን ግን ማጣራት አልቻልኩም ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ እንደ ዋነኛ ምክንያት የጠቀሰው አንዳንድ ወገኖች ግጭት እና አለመረጋጋትን የሚያባብሱ የጥላቻ መልዕክቶችን ለማሰራጨት እየተጠቀሙበት መሆኑን ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም በወቅቱ ለቢቢሲ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው ኢንተርኔት በአንዳንድ ወገኖች ለጥላቻ ንግግር ማሰራጫ መሳሪያ እንደተደረገ ጠቅሰዋል፤ በብሔሮችና በሃይማኖቶች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀስ መሳሪያ በመሆኑ እንዲቋረጥ መደረጉንም አመልክተዋል።

አቶ ዛዲግ ጨምረውም “መምረጥ የነበረብን በመረጃ ነጻ ፍሰት እና በሕዝባችን ሕይወት መካከል ነበር፤ በዚህም ለሰው ልጅ ሕይወት ቅድሚያ ሰጥተናል” ብለው የተወሰደው እርምጃ የዜጎችን ደኅንነት ከመጠበቅ አንጻር መሆኑን አመልክተዋል።

የአገሪቱ ባለስልጣናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጣቸው ከተለያዩ ወገኖች ትችት እና ወቀሳ ሲቀርብባቸው የሰነበተ ሲሆን፣ ምላሻቸው “የነበረው አለመረጋጋት ወደነበረበት ሲመለስ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ይቀጥላል” የሚል ነበር።

እነሆ ባለፈው ሳምንት የዋይ-ፋይ አግልግሎት ዛሬ ደግሞ የሞባይል ኢንርተኔት አገልግሎት በበርካታ ቦታዎች ላይ ወደ ሥራ መመለሱ ተነግሯል።


የዜና ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …