መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / አማን እና ቤተልሔም የጽሕፈት መሣርያዎች አቅራቢ

አማን እና ቤተልሔም የጽሕፈት መሣርያዎች አቅራቢ

ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2015 ዓ.ም. በአቶ አማን እና ወ/ሮ ቤተልሔም ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የስቼሽነሪ እቃዎችን እንዲሁም ደግሞ ጠቅላላ የጅምላ ንግድ እና የጽዳት እቃዎች አቅራቢ ድርጅት ነው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ አማን ይሄንን የስቴሽነሪ እና ጽዳት እቃዎች አቅራቢ ድርጅት ከመመሥረታቸው በፊት ተቀጥረው ይሠሩ ነበር። ይሁን እና የሚያገኙት ክፍያ በቂ ባለመሆኑ በዘርፉ ተሰማርታ የምትሠራ አንድ ጓደኛ ስለነበረቻቸው ከእሷ ጋር ከተማከሩ በኋላ በሁለት መቶ ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ድርጅቱን መሥርተዋል።

ድርጅቱ ከተመሠረተ ገና ትንሽ ጊዜ ቢሆነውም ከመንግሥት እና ከግል ድርጅቶች ጋር ከዐሥር በላይ የሚሆኑ ሥራዎችን ዐብሮ በመሥራት በሚገባ አጠናቆ ማስረከብ ችሏል። መጀመርያ ላይ በተባለው ጊዜ እቃዎችን ያለምንም መጓተት ማስረከብ በመቻሉ ተጨማሪ ሥራዎችን መሥራት እንዲችል አድርጎታል።

የድርጅቱ መሥራች ወደ እዚህ ሥራ ሲገቡ በጣም ከባድ ነገር የዋጋ መጨመር እንደሆነ ገልጸዋል። ይህም ማለት ለሥራው ተዋውለው የሚያስገቡት ዋጋ ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ሥራቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደነበረው ገልፀዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ የተለያዩ መፍትሔዎችን ተጠቅመዋል፤ ለምሳሌ በዘርፉ የቆዩ የቢዝነስ ባለቤቶች ከልምድ ምን ያህል እንደሚጨምር ስለሚያውቁ ያንን ገምተው የጨረታ ዋጋ ያስገባሉ። ይህንን በመመልከት እነሱም ገበያውን በማጥናት የዋጋ ማስተካከያ አድርገዋል። ሁለተኛው ደግሞ ከጓደኛቸው ባገኙት ምክር 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት ቢጠቀሙ ብዙ ጨረታዎችን እንደሚያገኙ ስለነገረቻቸው ይህንንም በመጠቀም ጨረታዎችን በቀላሉ መከታተል ችለዋል። ሦስተኛው ደግሞ ቢዝነስ ካርድ በመጠቀም እና ራሳቸው መሥራች አባላቱ በር ለበር በመንቀሳቀስ ነው ሥራዎችን የሚሠሩት። በዚህም ድርጅቱ ለሦስት ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በብዛት ጨረታ በመወዳደር ነው። ጨረታ ሲያሸንፍ  የሚያውቃቸው አስመጪዎች ስላሉ ከነሱ እቃውን በማስመጣት ወይም  በመረከብ ሥራውን ያከናውናል። በብዛት ደግሞ ጤና ጣቢያዎች፣ ክፍለ ከተሞች እና አንዳንድ የክልል ቢሮዎች በሚያወጧቸው ጨረታዎች  ላይ በመሳተፍ ነው ሥራዎችን የሚሠራው። በዚህም እስከ አሁን ድረስ የሚመጣውን ትዕዛዝ በሙሉ ማቅረብ በመቻል ጥሩ የሚባል የአፈጻጸም ታሪክ አለው። ከዚህ በኋላም ለሚመጣ ትዕዛዝ በፈጠረው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር የገበያ እና የሥራ ትስስር ማንኛውንም ትዕዛዝ በበቂ መጠን የማቅረብ አቅም አለው።

ምክር

ወደ እዚህ የሥራ መስክ የሚገባ ሰው በጣም ታጋሽ እና ተስፋ የማይቆርጥ መሆን አለበት። ምክንያቱም ሥራው ልፋት አለው ለምሳሌ ጨረታ ሲሳተፍ ሳምፕል መበተን፣ ዋጋ ማጣራት፣  እቃ መፈለግ፣ ወዘተ ይኖርበታል። ይህም ሆኖ ደግሞ ላይሳካ ይችላል ወይ ደግሞ የእቃው ዋጋ ከነበረው ይወደዳል፤ ስለዚህ ይህንን ሁሉ ለመቋቋም የሚችል መሆን አለበት ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

ዕቅድ

አማን እና ቤተልሔም ስቴሽነሪ ወደ ፊት አሁን ያለውን የወረቀት መወደድ ለመቋቋም ወረቀት ወደ ሀገር ቤት የማስመጣት ዕቅድ አለው።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …