መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ኒዮን ቢልዲንግ ኮንትራክተር

ኒዮን ቢልዲንግ ኮንትራክተር


ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሁሴን ፍቃዱ የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አጠቃላይ ኮንስትራክሽን፣ ሕንጻ ግንባታ እና የውሃ ሰፕላይ ሥራዎችን ይሠራል።

ድርጅቱ ከሚሠጣቸው አገልግሎቶች አንዱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አጠቃላይ የሕንጻ ግንባታ ሲሆን፤ እንዲሁም በውሃ አቅርቦት ዙሪያ ደግሞ የከተሞች የውሃ ሰፕላይ ሥራዎች እንደ አጠቃላይ፣ በተለይ ደግሞ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሥራዎች ላይ አገልግሎቱን ይሠጣል።

ድርጅቱ ካጠናቀቃቸው ፕሮጀክቶች መሃከል

  • የዲላ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት
  • የአዳማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀት እና የአዳማ ከተማ ቢሮ ግንባታ
  • ሞጣ ላይ የሃይማኖት ተቋም ግንባታ
  • አሁን ደግሞ በአፋር አሳይታ የውሃ ሥራ ፕሮጀክት ሥራ እየሠራ ይገኛል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሁሴን ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት በሲቪል መሃንዲስነት ተምረው ከተመረቁ በኋላ ለዐሥር ዓመታት በዘርፉ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተዋል። በመቀጠልረጅም ጊዜ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ብዙ ልምድ እና ተሞክሮ ካካበቱ በኋላ በራሳቸው መሥራት የሚችሉበት የብቃት ደረጃ ሲደርሱ ኒዮን ቢልዲንግ ኮንትራክተር ድርጅትን መመሥረት ችለዋል።

ድርጅቱ የሚሠጣቸውን የፕሮጀክቶች የማጠናቀቅ አቅም በማሳደግ አሁን ከኮቪድ በኋላ ባለው ሁኔታ አማካይ የድርጅቱ ገቢ አርባ ሁለት ሚሊዮን ብር ደርሷል። ይህም ሊሆን የቻለው ድርጅቱ የተሰጠውን ፕሮጀክት በተባለው ስምምነት መሠረት በጊዜ በማጠናቀቁ እና የአቶ ሁሴን አስተዋፅዖ ትልቁን ቦታ እንደሚወስድ የድርጅቱ መሥራች ተናግረዋል። በዚህም ለዐሥራ ሁለት ቋሚ ሠራተኞች እና እንደ ሥራው ሁኔታ ለሚጨመሩ ሠላሳ አምስት የሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ድርጅት ነው።

በዚህን ጊዜ ድርጅቱ እየገጠሙት ካሉ ችግሮች አንደኛ የሰው ኃይል ችግር ነው። ሥራ መሥራት የሚችል ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ሰው ማግኘት ከባድ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ሁሉም ላይ ያለ ችግር ሲሆን ይህም የማቴሪያል ዋጋ መወደድ ነው። ድርጅቱ እነዚህን ችግሮች እንደ ጊዜያቸው እና እንደሚከሠቱበት ቦታ አስፈላጊውን መፍትሔ በመስጠት እየተሻገረ ይገኛል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ባመቻቸው የከፍታ ፓኬጅ የጨረታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎችን በመከታተል እና በመሳተፍ ነው።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮሮና ጊዜ ድርጅቱ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አልነበረውም፤ ቆሞ ነበር። በፊት በሠራቸው ሥራዎች አኝይቶ የነበረውን ገንዘብ ተቀማጭ በመጠቀም የኮሮናን ጊዜ ማለፍ ችሏል። አሁን ነገሮች ጥሩ ላይ እንደሆኑ የድርጅቱ መሥራች ገልጸዋል።

ምክር

አቶ ሁሴን  ከተሞክሯቸው እንደሚናገሩት  አንድ ሰው አስፈላጊውን እውቀት ካካበተ በኋላ ምንም ችግር ሲመጣ ረጋ ብሎ በማጤን፣ ተስፋ ሳይቆርጥ መሥራት የሚችል ከሆነ የራስ ሥራ ያዋጣል። ይህም የሚፈልገውን ፕሮጀክት መርጦ እና አቅዶ እንዲሠራ ያደርገዋል። ስለዚህ ጠንካራ ለሆኑና እና ተስፋ ለማይቆርጡ ሰዎች የግል ሥራ የተሻለ እንደሆነ ይመክራሉ።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …