መነሻ / የቢዝነስ ዜና / ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ጀምሮ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ቅናሽ ሊያደርግ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ጀምሮ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ቅናሽ ሊያደርግ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት እና በድምፅ ጥቅል አገልግሎቶቹ ላይ ቅናሽ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ። ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ ቅናሽ የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ነውም ተብሏል።

ይህንን ያሳወቁት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የድርጅቱን የ3 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እና የ2013 በጀት ዓመትን ዋና የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

በመግለጫቸውም በኢንተርኔት ጥቅል ላይ 35 በመቶ፣ እንዲሁም በድምፅ ጥቅል ላይ የ29 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ገልፀዋል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

በተጨማሪም፣ የሞባይል ድምፅ እና ዳታ ጥምር አገልግሎት ላይ 28 በመቶ፣  እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይ 21 በመቶ፣ በፕሪሚየም ያልተገደበ የዳታ ጥቅል አገልግሎት ላይ 21 በመቶ፣ እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምፅ እና ዳታ ጥቅል አገልግሎት ላይ 20 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

በፕሪሚየም ፕላስ ያልተገደበ የጥቅል አገልግሎት 16 በመቶ እንዲሁም በሳተላይት አገልግሎት ላይ እስከ 61 በመቶ ቅናሽ መደረጉንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አንሥተዋል።

በቤትዎ ይቆዩ የጥቅል አገልግሎት ላይ፣ የፈረንጆቹ 2020 ማብቂያ ድረስ የሚቆይ የ59 በመቶ ቅናሽ ተደርጓልም ብለዋል።

ከዚህም በላይ፣ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአዲስ ዓመት የአደይ አበባ ጥቅል አገልግሎት ላይ 53 በመቶ ቅናሽ እንደተደረገ ገልጸዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …