ንሥር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አማ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግና በብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 626/2001 መሠረት ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኝ አስተማማኝ የፋይናንስ ተቋም ነው። ንሥር ለንግድ ሥራ፣ ለመኪና መግዣ፣ ለትምህርት ክፍያ፣ ለቤት መሥሪያ፣ ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለሌሎች ፍላጎትዎ ያበድራል።
ንሥር ለንግድ ሥራ እና ለመኪና መግዣ እስከ ብር 750,000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ድረስ ያበድራል። ለመበደር ምን ማድረግ አለብኝ?
ከንሥር ማይክሮፋይናንስ ብድር ለመበደር የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች
- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ (የዋስ እና የተበዳሪ ዋና እና 2 ኮፒ)
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዋና ምዝገባ ፍቃድ፣ የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ
- ዋስትናው መኪና ከሆነ ኦሪጅናል ሊብሬ እና ኮፒ፣ የኢንሹራንስ ውል የሻንሲ፣ የሞተር ቁጥር የመኪናው ግምት የያዘ ሰንጠረዥ ኮፒ፣ በተጨማሪም ኢንሹራንሱ በባለንብረቱና በንስር ስም መሆን አለበት እንዲሁም (ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያሳግዳል)
- ዋስትናው ቤት ከሆነ ኦሪጅናል ካርታ እና ኮፒ እንዲሁም (ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያሳግዳል)
- ለቤት ሥራ ብድር ከሆነ ኦርጅናል ካርታ እና ፕላን፣ የኢንሹራንስ ውል እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ
- በኮትራክተር ሥራ ላይ ላሉ የመሥሪያ ቦታው ኪራይ ከሆነ የቤት ኪራይ ውል ኮፒ እና የስራ ኮንትራት ውል ኮፒ
- ገቢና ወጪ የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት
- ከገቢዎች ግብር የተከፈለበት ደረሠኝና ክሊራንስ
- ለመኪና መግዣ ብድር ከሆነ የዋጋ ማቅረቢያ (ፕርፎርማ)
- የጋብቻ ሁኔታ የዋስ እና የተበዳሪ (ያላገባ ሰርተፍኬት ወይም የጋብቻ ሰርተፍኬት) ኮፒ እና የቲን ሰርተፍኬት
- 6 ፎቶግራፎች
- ተበዳሪው እና ዋስ እንዲሁም የሁለቱም የትዳር አጋሮች ካሉ የተቋሙ ውሎች ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል።
ከንሥር የማገኛቸው የብድር ዓይነቶች ምንድናቸው?
የብድር ዓይነት | የብድር ጣሪያ መጠን | አከፋፈል | የወለድ መጠን (በዓመት) |
---|---|---|---|
ለንግድ ሥራ | እስከ 750,000 ብር | ከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት | 32% |
ለመኪና መግዥያ | እስከ 750,000 ብር | ከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት | 28% |
ለቤት ማስጨርሽያ | እስከ 750,000 ብር | ከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት | 28% |
ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ | እስከ 40,000 ብር | ከ 1 ዓመት እስከ 2 ዓመት | 16% |
የንሥር የዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፎች አድራሻ እና ስልክ ቁጥሮች
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ደንበል ቅርንጫፍ | ደንበል ሲቲ ሴንተር፣ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205/A | +251 115 500 700/701 |
መገናኛ ቅርንጫፍ | ዘፍመሽ ግራንድ ሞል፣ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 115 | +251 116 674 666 |
በቅሎ ቤት ቅርንጫፍ | ሚክዎር ፕላዛ፣ ምድር ቤት ቁጥር 01 | +251 114 705 473 |
ፒያሳ ቅርንጫፍ | አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ህንጻ፣ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1/1/05 | +251 118 63 80 94 |
መርካቶ ቅርንጫፍ | አፊያ ቢዝነስ ሴንተር፣ 2ኛ ፎቅ | +251 112 732 759/733፣ +251 112 732 422 |
ለቡ ቅርንጫፍ | ሴፍዌይ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት፣ አንደኛ ፎቅ | +251 114 625 989 / 515 |
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ንሥር በሚያዘጋጀው ብሮሹር እና በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።