ንሥር ማይክሮፋይናንስ

ንሥር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አማ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግና በብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 626/2001 መሠረት ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኝ አስተማማኝ የፋይናንስ ተቋም ነው። ንሥር ለንግድ ሥራ፣ ለመኪና መግዣ፣ ለትምህርት ክፍያ፣ ለቤት መሥሪያ፣ ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለሌሎች ፍላጎትዎ ያበድራል።

ንሥር ለንግድ ሥራ እና ለመኪና መግዣ እስከ ብር 750,000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ድረስ ያበድራል። ለመበደር ምን ማድረግ አለብኝ?

ከንሥር ማይክሮፋይናንስ ብድር ለመበደር የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች

  1. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ (የዋስ እና የተበዳሪ ዋና እና 2 ኮፒ)
  2. የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዋና ምዝገባ ፍቃድ፣ የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ
  3. ዋስትናው መኪና ከሆነ ኦሪጅናል ሊብሬ እና ኮፒ፣ የኢንሹራንስ ውል የሻንሲ፣ የሞተር ቁጥር የመኪናው ግምት የያዘ ሰንጠረዥ ኮፒ፣ በተጨማሪም ኢንሹራንሱ በባለንብረቱና በንስር ስም መሆን አለበት እንዲሁም (ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያሳግዳል)
  4. ዋስትናው ቤት ከሆነ ኦሪጅናል ካርታ እና ኮፒ እንዲሁም (ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያሳግዳል)
  5. ለቤት ሥራ ብድር ከሆነ ኦርጅናል ካርታ እና ፕላን፣ የኢንሹራንስ ውል እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ
  6. በኮትራክተር ሥራ ላይ ላሉ የመሥሪያ ቦታው ኪራይ ከሆነ የቤት ኪራይ ውል ኮፒ እና የስራ ኮንትራት ውል ኮፒ
  7. ገቢና ወጪ የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት
  8. ከገቢዎች ግብር የተከፈለበት ደረሠኝና ክሊራንስ
  9. ለመኪና መግዣ ብድር ከሆነ የዋጋ ማቅረቢያ (ፕርፎርማ)
  10. የጋብቻ ሁኔታ የዋስ እና የተበዳሪ (ያላገባ ሰርተፍኬት ወይም የጋብቻ ሰርተፍኬት) ኮፒ እና የቲን ሰርተፍኬት
  11. 6 ፎቶግራፎች
  12. ተበዳሪው እና ዋስ እንዲሁም የሁለቱም የትዳር አጋሮች ካሉ የተቋሙ ውሎች ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል።

ከንሥር የማገኛቸው የብድር ዓይነቶች ምንድናቸው?

የብድር ዓይነትየብድር ጣሪያ መጠንአከፋፈልየወለድ መጠን (በዓመት)
ለንግድ ሥራእስከ 750,000 ብርከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት 32%
ለመኪና መግዥያእስከ 750,000 ብርከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት 28%
ለቤት ማስጨርሽያእስከ 750,000 ብርከ350,000 ብር በላይ ከሆነ በ3 ዓመት 28%
ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያእስከ 40,000 ብርከ 1 ዓመት እስከ 2 ዓመት16%

የንሥር የዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፎች አድራሻ እና ስልክ ቁጥሮች

ቅርንጫፍ አድራሻስልክ ቁጥር
ደንበል ቅርንጫፍደንበል ሲቲ ሴንተር፣ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205/A+251 115 500 700/701
መገናኛ ቅርንጫፍዘፍመሽ ግራንድ ሞል፣ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 115+251 116 674 666
በቅሎ ቤት ቅርንጫፍሚክዎር ፕላዛ፣ ምድር ቤት ቁጥር 01+251 114 705 473
ፒያሳ ቅርንጫፍአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ህንጻ፣ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1/1/05+251 118 63 80 94
መርካቶ ቅርንጫፍአፊያ ቢዝነስ ሴንተር፣ 2ኛ ፎቅ+251 112 732 759/733፣
+251 112 732 422
ለቡ ቅርንጫፍሴፍዌይ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት፣ አንደኛ ፎቅ+251 114 625 989 / 515

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ንሥር በሚያዘጋጀው ብሮሹር እና በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …