ዋን ማይክሮፋይናንስ

ዋን ማይክሮ ፋይናንስ ቀደም ሲል ለታ ማይክሮ ፋይናንስ በመባል ይታወቅ የነበረ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው። በብሔራዊ ባንክ ሕግ እና ደንብ መሠረት በአዋጅ ቁጥር 40/1996 (በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 626/2009) የተቋቋመ ሲሆን የማይክሮ ፋይናንስ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጥቶት ጥቅምት 28 ቀን 1997 (29 October 2004) ዓ.ም. ሥራ ጀምሯል።

“ንግድዎትን ወደላቀ ደረጃ ያሳድጉ”

ዋን ማይክሮፋይናንስ፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የፈቃድ ቁጠባ
  • ለብድር አገልግሎት የሚውል ቁጠባ
  • ያለመያዣ የሚሰጥ ዲጂታል የብድር አገልግሎት
  • ለሥራ ማስኬጃ እንዲሁም ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ የውል በተመጣጣኝ ወለድ የሚሰጥ የዐጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ብድር
  • የመጀመሪያ ብድር ሠላሳ ሺህ ብር ሲሆን፣ ለዚህም የንግድ ፈቃድ እና የመኖሪያ አድራሻ አዲስ አበባ ወይም ድርጅቱ አካባቢ መሆን ያስፈልጋል
  • በቀጣይ ለመበደር የተበደሩትን ብድር በአግባቡ መመለሱ ከተረጋገጠ ሌላ ተጨማሪ ብድር መበደር ይችላሉ።
  • የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ
  • የአየር ሰዓት መሙላት
  • ሌሎች የዲጂታል የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶች

ዋን ማይክሮፋይናንስ፦ አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

  • ዩኒቲ ፓርክ የመኪና ማቆሚያ አጠገብ፣ ፓላስ የንግድ ማዕከል፣ 4ኛ ፎቅ

ስልክ

  • +251 116 595363
  • +251 911087118
 

ኢሜይል

  • info@onemicrofinancesc.com

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ  የተዘጋጀው ዋን ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …