መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሬድዋን ተማም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት

ሬድዋን ተማም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት

ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም. በዐሥር መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ የኪችን ካቢኔቶችን በዋናነት በማምረት ላይ ይገኛል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • ኪችን ካቢኔት እና ዲስፕሌዮች(የእቃ ማሳያ ሳጥኖች)
  • በሮች እና ወንበሮች
  • ቡፌዎች እና አልጋዎች
  • ድሬሲንግ ቴብሎች
  • የግድግዳና የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ቁምሳጥኖች
  • ሌሎች አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን በጥራት ያመርታል

    ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሬድዋን ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት በዘርፉ ተቀጥረው አምስት ዓመት ሠርተዋል። አቶ ሬድዋን በተቀጠሩበት ድርጅት ውስጥ እየሠሩ በነበረበት ወቅት አንዳንድ ሥራዎችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ በትርፍ ጊዜአቸው ሲሠሩ ቆይተዋል። ለአንድ ዓመት በዚህ ሁኔታ ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ ተያያዥ በግላቸው ለመሥራት የሚያስችላቸውን መሠረታዊ መሣሪያዎች በጊዜዎች ሂደት ካሟሉ በኋላ በራሳቸው ሬድዋን ተማም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ሊመሠርቱ ችለዋል።

ድርጅቱ ሃምሳ የኪችን ካቢኔት ምርቶችን በአንድ ሳምንት ውስጥ የማምረት አቅም አለው። በእንጨት ሥራ የዐሥራ ሦስት አመት የሥራ ልምድ አካብቷል። ድርጅቱ ሥራ ሲጀምር ምንም አይነት መነሻ ካፒታል ያልነበረው ሲሆን አሁን ላይ ግን ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ካፒታል አፍርቷል። እንዲሁም ለሦስት ቋሚ ሠራተኞች እና ከአምስት እስከ ዐሥር ለሚደርሱ ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፈጠር ችሏል። በተጨማሪም ሁለት የማምረቻ ቦታዎችን አንድ በአየር ጤና ኢንዱስትሪ መንደር ሁለተኛ ደግሞ ጀሞ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 77 ከፍቶ እያመረተ ይገኛል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች ዋጋ በከፊል

  • ኪችን ካቢኔት እንደ ሚሠራበት እቃ ቢለያይም በካሬ ከአምስት ሺህ ብር እስከ ስምንት ሺህ ብር ይሠራል።
  • በሮችን ደግሞ ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ አሥራ አራት ሺህ ብር ድረስ በሮችን ያመርታል።

አቶ ሬድዋን ሁሴን ወደ እንጨት ሥራ የገቡት በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው። አንዱ የሙያው ትልቅ ፍላጎት ከልጅነታቸው ጀምሮ ነበራቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሚሊኒየም ወቅት በዘርፉ ከፍተኛ የሥራ እድል ስለነበር እና የሚያዋጣ የሥራ ዘርፍ ስለነበር ወደ ዘርፉ እንደገቡ አስረድተዋል።

አቶ ሬድዋን ሁሴን አሁን ላሉበት ደረጃ የደረሱት ብዙ ችግሮችን እና ተግዳሮቶችን አልፈው ነው። ለምሳሌ ተቀጥረው በሠሩበት ወቅት ቀን ላይ ብቻ ነበር የሚሠሩት አሁን ግን ሌሊትም እየገቡ ይሠራሉ። እንዲሁም አሁን ላይ እየመጡ ያሉ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ገበያ ላይ መግባታቸው ሥራው ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል። ሌላው አስከፊ ችግር ድርጅቱ ላይ የእሳት አደጋ ተነስቶ ብዙ ንብረቶች ወደመው ነበር፤ በዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ ጠንከረው በመሥራታቸው ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱት።

የድርጅቱ መሥራች እንዳንድ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸው ለድርጅታቸው እድገት አስተዋፅዖ እንዳለው ጠቅሰዋል፤ ለምሳሌ የጃፓን ካይዘን ስልጠና። ድርጅቱ ሥራዎችን በዋናነት የሚሠራው በሰው በሰው ሲሆን በመቀጠል ደግሞ በቢዝነስ ካርድ በመጠቀም ነው።

ምክር እና እቅድ

አቶ ሬድዋን አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚገቡ ሰዎች የሚከተለውን ብለዋል። ሙያውን በደንብ አውቀው ይጀምሩ፤ ምንም ችግር ቢያጋጥማቸው ተስፋ ሳይቆርጡ እንዲሠሩ፤ በመጨረሻ ደግሞ የሚያመርቱን ምርት በጥራት ያምርቱ ይህ ወሳኝ ነው ብለዋል። ጥራት ካለው ደንበኛ ይመጣል ከሌለው ግን ጭራሽ ያለውም ይሄዳል ስለዚህ ምርታቸው ላይ በተቻለ መጠን በጥራት ያምርቱ ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

ድርጅቱ ወደ ፊት የምርት ማሳያ ሱቆችን የመክፈት እና እንዲሁም የብረት ሥራዎችን ለመሥራት እቅድ አለው። በከፍታ ቴሌግራም ቻናል ላይ የሚለቀቁ ጨረታዎችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …