መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ መረጃ
kefta

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ መረጃ

ጥቃቅን / አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ምን ማለት ነው?

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከጠቅላላ ሃብት እና ከሰው ኃይል አንፃር፣ በየዘርፉ እንደሚከተለው ይተረጎማል።

ዘርፎች እና ንዑስ ዘርፎች

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሁለት ዋና ዘርፎች (ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት) የሚከፈሉ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ሥር ደግሞ የሚከተሉት ዋና ዋና ንዑስ ዘርፎች ይገኛሉ።

  1. ኢንዱስትሪ
    • ማኑፋክቸሪንግ
    • ኮንስትራክሽን
    • ማዕድን
  2. አገልግሎት
    • ችርቻሮ ንግድ
    • ትራንስፖርት
    • ሆቴልና ቱሪዝም
    • የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥገና አገልግሎት
  1. ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ
    • ጠቅላላ ሃብት
      • ለኢንዱስትሪ ዘርፍ – ከ 100 ሺህ ብር ያልበለጠ (ለጀማሪ ከ 50 ሺህ ብር ያልበለጠ)
      • ለአገልግሎት ዘርፍ – ከ 50 ሺህ ብር ያልበለጠ (ለጀማሪ፡ ከ 40 ሺህ ብር ያልበለጠ)
    • የሰው ኃይል
      • ባለቤት እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ እስከ 5 ሰው ቀጥሮ የሚያሠራ
  2. አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
    • ጠቅላላ ሃብት
      • ለኢንዱስትሪ ዘርፍ – ከ 100,001 እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር
      • ለአገልግሎት ዘርፍ – ከ 50,001 እስከ 500,000 ብር
    • የሰው ኃይል
      • ከ 6 እስከ 30 ሰዎች ቀጥሮ የሚያሠራ

ይህንንም ይመልከቱ

በኮቪድ-19 ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የሚውል 207 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

ዛሬ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት ላይ በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር …