liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት በ1989 ዓ.ም. ተመሠረተ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለተቋሙ የሰጠው የፈቃድ ቁጥር MFI/034/2011 ሲሆን የንግድ ምዝገባ ቁጥሩ ደግሞ 06/2/06393/96 ነው። ተቋሙ ከቀደምት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ24 ዓመት በላይ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ ተቋሙ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በቀደሞው የደቡብ ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 26 ቅርንጫፎች ከ70,000 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች የብድር፣ የቁጠባ እና የብድር የሕይወት መድን ኢንሹራንስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ቁጠባ ነገን የተሻለ ያደርጋል!!!

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

ተቋሙ ኅብረተ ሰቡ ሀብት አፍርቶ የነገ ባለተስፋ እንዲሆን የቁጠባ አገልግሎት ይሰጣል። የቁጠባ አገልግሎት ዓይነቶች
  1. መደበኛ ቁጠባ (Ordinary Saving)
  2. የቤት ቁጠባ (House Saving)
  3. ተስፋ የልጆች ቁጠባ (Tesfa Children Saving)
  4. የሳጥን ቁጠባ (Box Saving)
  5. በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ከፍተኛ ወለድ የሚያስገኝ ቁጠባ (Time Deposit)
  6. የተቋማት ቁጠባ (Institutional Saving)
  7. ለኅብረተ ሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ እድር፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ማኅበራት እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማትየሚቆጥቡት ቁጠባ ነው።
ለጊዜ ገደብ ቁጠባ ዓመታዊ ወለድ እስከ 13% የሚታሰብ ሲሆን ለሌሎች ቁጠባዎች ደግሞ ከ 8 - 9.5% ድረስ ይታሰባል! በተቋሙ መቆጠብ በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ኅብረተ ሰብ ብድር አግኝቶ የተሻለ ሥራ እንዲሠራ ማገዝ ስለሆነ የመንፈስ ዕርካታ ይሰጣል።
ተቋሙ የገንዘብ ዕጥረት ላጋጠማቸው፣ ሠርቶ ለመለወጥ ጥረት ለሚያደርጉና ኑሯቸውን ለማሻሻል ፍላጎት ላላቸው የብድር አገልግሎት ይሰጣል። ተቋሙ የሚሰጣቸው የብድር አገልግሎት ዓይነቶች፦
  1. የሴት ሥራ ፈጣሪዎች ብድር (WEDP Loan)
  2. የጥቃቅን እና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር (MSE Loan)
  3. የግል ብድር (Individual Loan)
  4. አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር (SME Loan)
  5. የቤት ብድር (Housing Loan)
  6. ለንጹህ ውሃ አቅርቦት እቃዎች መግዣና ለመጸዳጃ ቤት ግንባታ ብድር (WASH Loan)
የብድር መጠኑ እስከ ብር 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን  ዐምስት መቶ ሺሕ ብር) ድረስ ይደርሳል።

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ፣ ዳሩሌ ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ

ስልክ

011 1 570 787

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ልዪ የገንዘብ የእገዛ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ae-logo

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

ኅብረት ሥራ ማኅበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ …