መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ከወጪ ንግድ ወደ 4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቀደ
export-containers

ከወጪ ንግድ ወደ 4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቀደ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው የ2013 በጀት አመት ከ ወጪ ንግድ 3.91 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት በዕቅድ መያዙን አስታወቀ። ከዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍና ክትትል ከሚያደርግባቸው የግብርና 2.918 ቢሊዮን እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ምርቶች 587.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚጠበቅ ጨምሮ አስታውቋል ፡፡

ከምርት አቅርቦት እስከ ወጪ ንግድ ባለው የግብይት ሰንሰለት በየደረጃው ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት ከዘርፉ የወጪ ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማሳደግ የሚለውን ዓላማ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው መነሻ እቅድ የተለያዩ ትንተናዎችን ከግምት አስገብቶ የተሠራ ነው።  የአምስት ዓመታት የግብርና ምርቶች የምርት እና ምርታማነት ትንተና፣ የአምስት ዓመታት የወጪ ንግድ የዕቅድ አፈፃፀም ትንተና፣ የ2012/13 ምርት ዘመን የግብርና ምርቶች አቅርቦት ትንበያ ግምት፣ የግብርና ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ያላቸው ፍላጎት፣ የዓለም ገበያ የግብርና ምርቶች ዋጋ ትንበያ፣ ከ2012 በጀት ዓመት የዞረ የወጪ ንግድ ምርቶች ክምችት ትንተና፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የግብርና ምርቶች ጥሬ ግብዓት ፍላጎት ትንተና፣ የወጪ ግብርና ምርቶች የብጣሪ/ሪጀክት መጠን ትንተና እና የኮቪድ-19 ወረርሽን ለግብርና ምርቶች ያለው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅእኖ የሚሉትን ነጥቦች ለዕቅዱ ዝግጅት በመነሻነት ከታዩ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል፡፡

ዕቅዱ በታሳቢነት ያስቀመጣቸው አመላካቾች አዎንታዊነትን ተከትሎ እቅዱን ለማሳካት የምርት አቅርቦትንና ጥራትን ማሳደግ፣ የአሰራር ስርዓቶችን ማሻሻል፣ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ የፋይናንስ ስርዓት ማሻሻል የህገ-ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ መቆጣጠር እና የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚተገበሩ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …