ዮዲ ሳሙና

ዮዲ ሳሙና የተመሠረተው በአቶ ተስፋዬ በፍቃዱ እና አራት መሥራች አባላት በ 2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈሳሽ ሳሙና እና ደረቅ ሳሙና ምርቶችን ያመርታል።

የሚያመርታቸው ምርቶች

  • አጃክስ
  • ፈሳሽ ሳሙና
  • ቶይሌት ቦል (የወንዶች ሽንት ቤት ላይ ያለች ኳስ መሰል ሽታ ማስወገጃ)
  • የልብስ ሳሙና
  • በረኪና
  • አጠቃላይ የሳሙና ሥራዎችን

ምሥረታ፣ ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ተስፋዬ በደረቅ ሳሙና ሥራ ዘርፍ ከመሠማራታቸው በፊት በቴራዞ ሥራ ላይ ተሠማርተው ምርት ሲያመርቱ ቆይተዋል። ይሁና እና በአንድ ወቅት ወደ ክልል ከተማ ለሥራ ሄደው በተነሳው የሰላም ችግር ኮንትራክተሩ ብዙ ኪሳራ ደርሶበት እሳቸውም የማምረቻ ማሽኖቻቸውን ስለወደሙ እንደምንም ብለው ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ችለዋል። በዚህ ችግር ምክንያት የበፊቱን ሥራ መሥራት የማይታሰብ ስለነበር ተስፋ ሳይቆርጡ ምን ብሠራ ያዋጣኛል ብለው ካሰቡ በኋላ ወቅቱ ኮቪድ በውጭ ሀገራት በጣም እየተስፋፋ ስለነበር ንጽህና መጠበቂያ ምርት ባመርት ያዋጣኛል ብለው ይወስናሉ።  በመቀጠልም እንደምንም ገንዘብ በማሰባሰብ ህንድ ሀገር በመሄድ የሳሙና አሠራርን በሚገባ ከተማሩ በኋላ አንድ ማሽን ይዘው ሀገር ቤት ይመጣሉ። ያመጡትን ማሽን ትንሽ እንደሠሩበት እሱን ይሸጡና በራሳቸው የተሻለ ምርት ማምረት የሚችል ማሽን ዲዛይን በመፍጠር ከህንድ ካመጡት ማሽን የተሻለ ምርት የሚያመርት ማሽን ሠርተው የተሻለ ምርት እያመረቱ ይገኛሉ።

ድርጅቱ በሳሙና ሥራ ዘርፍ ሊሠማራ የቻለው አንደኛ ሳሙና አላቂ ስለሆነ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሁሉም ሰው ስለሚጠቀመው እና ኮቪድ ስለመጣ በዚህ ዘርፍ ብንሰማራ የተሻለ ነገር ለሀገርም ማበርከት ይቻላል በሚል ይህን ዘርፍ እንደመረጡ የድርጅቱ መሥራች ያስረዳሉ።

ዮዲ ሳሙና በቀን አንድ መቶ ሃያ አምስት ካርቶን ሳሙና ወይም በቀን አሥራ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሳሙናዎችን ያመርታል። ይህንንም ምርት አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ አንድ ካርቶን በሦስት መቶ ስልሳ ብር እየሸጠ ይገኛል። በነጠላ ደግሞ የአንዱ አጃክስ ዋጋ በስድስት ብር ዋጋ ለገበያ ያቀርባል። ድርጅቱ አሁን ምርቱን ለአከፋፋዮች ሲሆን የሚያቀርበው፣ ብዛት መውሰድ የሚፈልግ ተጠቃሚ ግን ከመነሻ ዐሥር ካርቶን ጀምሮ መግዛት ይችላል።

ድርጅቱ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው አንደኛ ደንበኞች ራሳቸው ምርቱን ፈልገው ይመጣሉ፣ ሁለተኛ  ድርጅቱ ራሱ ታርጌት ደንበኞች የሚላቸው ጋር በመሄድ ይሸጣል ሌላው ደግሞ በከፍታ በተመቻቸው የ2merkato.com የቢቱቢ (B2B) የኦንላይን መድረክ ላይ ያለውን የዮዲ ሳሙናን ፕሮፋይል እያዩ የሚደውሉ ሰዎች አሉ፤ በዚህም ሥራዎችን ሠርቷል። ይሁን እና አሁን የሚደውሉት ሰዎች ጥያቄአቸው ቴራዞ ነው ይህን እኛ ቀይረናል ብለን እንነግራቸዋልን። ሌላው ደግሞ አንዳንድ የግል የሽያጭ ሠራተኞች በራሳቸው እየመጡ ምርት ወስደው የሚሸጡ አሉ።  ሌላው ደግሞ አንዳንድ የኮንትራት ሥራ በመሥራት አሁን ራሱ ለንፋስ ስልክ/ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሥራ ለመሥራት በሂደት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ድርጅቱ ሥራ ሲጀምር በዐሥራ ዐምስት ሺህ ብር ካፒታል ሲሆን አሁን ላይ ካፒታሉ አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር ደርሷል። በውስጡም ለሰባት ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮሮና ጊዜ የነበረው ተፅዕኖ ከባድ ስለነበረ ሥራ በጣም ቀዝቅዞ ነበር። በዚህ ወቅት ሳኒታይዘር ለመሥራት እቅዱ ቢኖርም ፈቃድ ለማግኘት፣ ደረጃ መዳቢ እና ጥራት ቁጥጥር እየተባለ ሂደቱ ስለበዛ ያንንም በታሰበለት ጊዜ ሳይሠራ ቀርቷል።

ምክር እና እቅድ

በዚህ የሥራ ዘርፍ ሥራ ለመጀመር እቅድ ያላቸው ሰዎች ስለ አሠራሩ ሥልጠና መውሰድ ግዴታ ነው። ይህንንም ሥልጠና የንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ይሰጣል፤ ድርጅቱም ከኮሌጁ ጋር አብሮ በመሥራት ድጋፎችን አግኝቷል። ቀጥሎ ጥሩ ኬሚስት ያስፈልጋል፤ ካልሆነ ግን ሥራውን ወደ ኪሣራ ይዳርጋሉ በመጨረሻ ደግሞ ማሽኖቹ ጥራት ያላቸው እና የተፈተሹ መሆን አለባቸው። የሥራ ዲሲፒሊን ያስፈልጋል፤ የካይዘን አጠቃቀም በጣም አስፈላጊ ነው።

ድርጅቱ ከማሽን ማዘመን ጀምሮ ራሱን በማማሻል ብዙ ምርቶችን ለማምረት በተቻለ መጠን ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ራሱን እያሳደገ ይገኛል። በመጪዎቹ ዐምስት ዓመታት ውስጥ አቅሙነ በማሳደገ የሚያመርታቸውን ምርቶች የመጨመር እና ተጓዳኝ ሥራዎችን የመሥራት እቅድ አለው።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …