መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ዮሴፍ እና መስፍን የአልሙኒየም ሥራ

ዮሴፍ እና መስፍን የአልሙኒየም ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮሴፍ ንጉሤ እና በጓደኛቸው 2011 ዓ.ም. የኅብረት ሽርክና ማኅበር ሆኖ ነው። ማኅበሩ አጠቃላይ የአልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በተጠጣጣኝ ዋጋ የማምረት እና የመገጣጠም ሥራ ይሠራል።

ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የአልሙኒየም በርና መስኮት ማምረትና መግጠም
  • በአልሙኒየም የሚሠሩ የቢሮ ፓርቲሽኖች ማምረትና መግጠም
  • በአልሙኒየም የሚሠራ  curtain wall ማምረትና መግጠም
  • በአልሙኒየም የሚሠራ የሃንድሪል ሥራ
  • የክላይዲንግ ሥራ
  • ፍሬምለስ ፓርቲሽኖች ሥራ

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ማኅበሩ አብዛኛው የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የእጅ ዋጋ (labour) ብቻ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱና እንደገበያው ሁኔታ ማቴሪያሎችን በማቅረብ አገልግሎት የመስጠት ሥራ ይሠራል።

አቶ ዮሴፍ ወደ አልሙኒየም ሥራ ከመግባቻቸው በፊት በቤተሰባቸው የኮንስትራክሽ ሥራ ውስጥ ለተወሰኑ ዓመታት ሠርተዋል። በመቀጠል ደግሞ የአልሙኒየም ሥራ ጥሩ እንደሆነ እየተረዱ ሲመጡ በዘርፉ ዕውቀት ለማዳበር በሌሎች የአልሙኒየም ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በመሥራት ወደ ስድስት ዓመት አሳልፈዋል። በቂ ልምድ ካካበቱ በኋላ በግላቸው ከጓደኛቸው ጋር በመሆን የአልሙኒየም ሥራ ከሚያውቋቸው ሰዎች ጋር በመነጋገር መሥራት ይጀምራሉ። ይህ ሲሆን ግን ንግድ ፈቃድ አልነበራቸውም ምክንያቱም ሥራው ገና ስለነበረ ዘርፍም አልነበረውም።

ድርጅቱ ትንሽ ሥራዎች በመሥራት ላይ እንዳለ አንድ የፊኒሺንግ ማሰልጠኛ ተቋም ትምህርቱን መስጠት ጀመረ። ይህ ተከትሎ ዘርፉ ዕውቅና ሲያገኝ ወረዳም ማደራጅት እና ፈቃድ መስጠት ጀመረ። አቶ ዮሴፍም በመሄድ ፈቃዳቸውን ካወጡ በኋላ ሥራዎችን በደንብ ለመሥራት ችለዋል።

ድርጅቱ የሥራ ፈቃድ ሲያገኝ በፊት በሰው በሰው የሚሠራቸው ሥራዎች የበዙ ስለመጡ እስከ ሃያ ለሚጠጉ ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሎ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችን ማሟላት ችሏል።  በዚህም የመሥራት አቅሙን ከመኖሪያ ቤቶች በማሳደግ አፓርታማዎችን መሥራት ጀምሯል፤ ለምሳሌ ሰንጋተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም በሚገባ ሠርቶ አጠናቅቋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ ከባድ ተፅዕኖ ነበረው። ሥራ በጣም ቀዝቅዞ የነበረ ሲሆን ሰውም አያሠራም። ጥሬ እቃም ጠፍቶ ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ እቃ በጣም ተወድዶ ነበር። ይህንንም ችግር ለማስታገስ ከማስተር ካርድ በመጣ የእፎይታ ብድር በመበደር ሊያሳልፉት ችለዋል። ከኮቪድ በኋላ ትንሽ የተሻለ ነገር ስለተፈጠረ የተበደሩትንም ብድር ከፍለው በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው አንድ በሰው በሰው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ከትልልቅ ድርጅቶች ሥራዎችን            በሰብ-ኮንትራት በመውስድ ሳይት ድረስ በመሄድ ነው። ድርጅቱ አሁን ባለው አቅም አራት ፎቅ የመኖሪያ ሕንጻ በሃያ ቀን ማጠናቀቅ ይችላል። እንዲፈጥን ከታሰበ ደግሞ አስፈላጊውን የሰው ኃይል በመጨመር በዐጭር ቀን ማጠናቀቅ ይቻላል።

ድርጅቱ ምንም ዓይነት ችግር ወይም አክል ሲገጥመው አባላቱ እርስ በርስ በመመካከር አስፈላጊም ከሆነ የሚያውቋቸውን ሰዎች በማማከር እየፈታ ይገኛል።

ምክር

“አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ሰዎች ከምንም ዓይነት ሱስ የፀዱ መሆን አለባቸው፤ ያለበለዚያ ሥራው ገንዘብ ቶሎ ስለሚያገዝኝ ሱስ ካለ ግን እዛው ያጠፉት አና ውጤታማ መሆን እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል። በመቀጠል ደግሞ ሠርተው ለማደግ እቅድ ያስፈልጋል፤ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ቢመጣም ጠንክረው መሥራት አለባቸው። ይህን ካሉ በኋላ ደግሞ ስለ ሥራው ትንሽ ትምህርት ያስፈልጋል፤ ወይም ደግሞ በዘርፉ ልምድ ኖራቸው ወደ ሥራው ቢቀላቀሉ ተገቢ ነው” አቶ ዮሴፍ ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ዮናታን ታደሰ እና ሦስት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት …