መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ከድር ተማም የቤት እና የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ የቤት መገልገያ እቃዎች መሸጫ

ከድር ተማም የቤት እና የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ የቤት መገልገያ እቃዎች መሸጫ

ከድር ተማም የቤት እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም. ነው።  ድርጅቱ አጠቃላይ ለቤት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ኤክትሮኒክስ እና የኪችን እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል።

ድርጅቱ የሚሸጣቸው እቃዎች

  • የስጋ፣ የሽንኩርት እና የጁስ መፍጫ ማሽን
  • የተለያየ መጠን ያላቸው የውሀ ማፍያዎች
  • የተለያየ መጠን ያላቸው የኤሊክትሪክ እና የሶላር አምፖሎች
  • የቡና መፍጫ ማሽኖች
  • የውሀ ፔርሙዞች
  • የኤሌክትሪክ ስቶቮች
  • የኤሌክትሪክ ስቶቮችን ማስጠቀም የሚችሉ ትልቅ አቅም ያላቸው ማከፋፈያዎች እና አጠቃላይ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃቆችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል።

 

ምሥረታና ዕድገት

አቶ ከድር ወደ ንግድ የገቡት በልጅነታቸው አባታቸው ስላረፉ እና እናቻቸውም ታመው ስለነበር በፊት ተማሪ  እያሉ ከትምሕርታቸው ጋር አብረው ሶፍት እና ማስቲካ እየሸጡ ቤተሰባቸውን ይረዱ ነበር። በተፈጠረው ችግር የቤተሰቡ ኃላፊነት እሳቸው ላይ በመሆኑ ትምሕርታችውን በማቆም ነው ወደ ንግድ ሥራ የገቡት። በዚህም ሥራ ብዙ ጊዜ በመቆየት የራሳቸውን ቤተሰብ ሊመሠርቱ ችለዋል።

ድርጅቱ አብዛኛውን ሥራ የሚሠራው ከደንበኞች በመተማመን ነው። ይህንንም ለደንበኞች ክሬዲት በመስጠት የአንድን እቃ ዋጋ በሁለት እና ሶስት ወር ክፍያ እንዲከፍሉ በማድረግ እና በዛ ያለ እቃ ከፈለጉ ደግሞ ከድርጅታቸው ወይም መሥሪያ ቤታቸው ደብዳቤ በማምጣት በተወሰነ ጊዜ በውሉ መሰረት እቃውን በመውሰድ የሚከፍሉበት ስምምነት ይሠራል። እንዲሁም በጣም ብዙ ትዕዛዝ ከመጣ እቃ ከሚያመጡበት ቦታ በእምነት እና ባንክ ከቆጠቡት በመሰብሰብ ምርቱን ለተጠቃሚ ያደርሳሉ። ድርጅቱ ማንኛውንም የቤት እና የቢሮ መገልገያ እቃ በበቂ ሁኔታ የማቅረብ አቅም አለው።

ድርጅቱን ሲመሠርቱ በአምስት መቶ ብር ሲሆን አሁን ሃምሳ ሺህ ብር ካፒታል ያለው ድርጅት ሆኑዋል። የድርጅቱ መሥራች የራሳቸው ህይወት ሊያሻሽሉ ችለዋል፤ እነዚህ ተስፋ ያለመቁረጥ እና ታታሪ ሠራተኛ የመሆን ውጤቶች ናቸው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ከድር ወደ ንግድ ሥራ ከገቡ ሰላሳ አመት ሆኗቸዋል። መርካቶ ነበር ሥራ የጀመሩት። በዚያን ወቅት መውደቅ እና መነሳት ነበረ፤  በተጨማሪም ወደ አረብ አገር ሄዶ የመሥራት አጋጣሚ ተፈጥሮ ስለነበር ለአራት አመት ከአገር ውጭ ሄደው ሲሠሩ ቆይተዋል። ከተመለሱ በኋላ በጥቃቅን እና አነስተኛ የመሥራት ዕድል በ1997 ዓ.ም. ሲጀመር ብዙ ሞከረው ነበር።  ከብዙ መመላስ እና ተስፋ ባለመቁረጥ ከሞከሩ በኋላ በ2005ዓ.ም. የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆኑ ችለዋል።

ድርጅቱ ምርቱን የሚያስተዋውቀው በደንበኞች ነው፤ ብዙ ሥራ የሚመጣው በሰው በሰው ነው። ስለዚህ ደንበኛ የተበላሸ እቃ እንኳን ቢያመጣ በስነ ሥርዓት ነው የሚስተናገደው፤ ምክንያቱም በሱ ምክንያት የሚቀረው ብዙ ስለሆነ ያንን በማሰብ ተቀብሎ በትክክል በማስተናገድ፣ ለደንበኛ ከፍተኛ ክብረ በመስጠት ነው እየሠራ የሚገኘው። ስለዚህ በንግድ ሥራ ለማደግ እና ለመስፋፋት መተማመን እና ደንበኛን ማክበር በጣም ወሳኝ እና ጠቃሚ እንደሆነ አቶ ከድር አስረድተዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮሮና ወረርሽኝ ተፅዕኖ ከባድ ነበር። ቢሆንም ድርጅቱ አልተዘጋም ምርቶቹ ለሕብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ፣ በተለይም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የውሀ ማፍላት አገልግሎት የሚሰጡ ማሽኖች ማኅበረሰቡ የሚፈልጋቸው ስለነበሩ እነሱን ስርጀቲ ያቀረ ነበር።  በተጨማሪም ከመጀመሪያዎቹ ማስክ ሻችፕች ነበሩ። ከጊዜ በሁዋላ ግን ማስክ ብዙ ቦታ መሸጥ ሲጀምር ድርጀቱ ወደበፊቱ ሥራው በመመለስ የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜን ሊያልፍ ችሏል።

ምክር እና እቅድ

በንግድ ሥራ ላይ በጣም ከባድ የሆነው ነገር የዋጋ መለዋወጥ ነው። ለምሳሌ አንድ እቃ ባመጣሁት ዋጋ ላይሸጥ ይችላል፤  ይህ ደግሞ ደንበኛን ያስቀራል ወይም ተመልሶ እንዳይመጣ ያደርጋል። ስለዚህ ደንበኛ እንዳይቀር በሚል የእቃው ዋጋ ሲቀንስ ማምጣት የተሻለ ነው። ያለበለዚያ ይገዛሉ ብሎ አምጥቶ ካልተገዛ እቃው ገንዘብ ይዞ ይቀመጣል፣ ኪሳራም ያስከትላል።

 

እቅዳቸው ልጆቻቸውን በሚገባ በማስተማር ትልቅ ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ማድረግ ነው። ይህንንም በሚገባ እየተውጡ ይገኛሉ።

ወደ ንግድ ሥራ የሚገቡ ሰዎች ሥራ ላይ የሚያበሳጭ እና የሚያሳዝኑ ነገሮች ይፈጠራሉ ስለዚህ ነገሮችን በልክ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ቀጥሎ በሥራ ሰዓት ሥራ ላይ መገኘት፣ ገንዘብ መቆጠብ፣ ወጪውን እና ገቢውን ማመጣጠን መቻል አለባቸው። ትልቁ ነገር ደግሞ ራሳቸውን ከሱስ ነጻ ማድረግ አለባቸው። ለሥራው ተገቢውን ክብር መስጠት መቻል እና ደንበኛን ማክበር አስፈላጊ ናቸው ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ከድር ፈጣሪን፣ ደንበኞቻቸውን፣ ወረዳውን እና ጎረቤቶቻቸውን በዚህ አጋጣሚ አመስግነዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …