sheger-mfi-logo

ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም

ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በብዙሃን የግል ባለሃብቶች እና በግል ኩባንያዎች የተቋቋመና በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተሞክሮና እውቀት ባካበቱ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ነው። በአሁኑ ወቅት ቅርንጫፎቹን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እና በሌሎች በክልሉ በሚገኙ ከተሞች በማስፋፋት የኅብረተ ሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን የመቅረፍ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

SHAGGAR ISIN WALIIN MIIDHAGA!
ኑ ከሸገር ጋር አብረን ነጋችንን ብሩህ እናድርግ!
BETTER TOGETHER!

ሽገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ዝርዝር መረጃ

  • ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • የባለአክሲዮኖችን መተዳደሪያ ደንብና ልዩ ልዩ መመሪያ ደንቦችን የሚቀበል
  • የመመዝገቢያ ክፍያ 5% እና ዝቅተኛውን የአክሲዮን ክፍያ 10,000 (አስር ሺህ) ብር እና ከዚያ በላይ መግዛት የሚችል
  • በማኅበር ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ
  • የአንድ ዕጣ (አክሲዮን) ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ሲሆን አንድ አባል ዝቅተኛ መግዛት የሚችለው 10 (ዐሥር) እጣዎችን ነው
  • ማንኛውም አባል ተጨማሪ አክሲዮን መግዛት ይችላል።

ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

መደበኛ ቁጠባ

ማንኛውም ሰው በፈለገው ጊዜ የሚቆጥበውና ወለድን ጨምሮ ማውጣት የሚችለው የቁጠባ ዓይነት ነው (7% ወለድ ይከፈልበታል)።

ወለድ አልባ ቁጠባ

አንድ ግለሰብ እንደፍላጎቱ የወለድ አልባ ቁጠባ አገልግሎት ማግኘት ይችላል።

በጊዜ የተገደበ ቁጠባ

በግለሰቦች እና ድርጅቶች ከ6 ወር በላይና ከ100,000 ብር ጀምሮ የሚቀመጥ ሂሳብ ሲሆን እንደ ተቀማጩ የገንዘብ መጠን እና ከሚቀመጥበት ጊዜ መነሻ ተድርጎ ከ 9%-13% ወለድ ይከፍላል።

የህጻናት ቁጠባ

እድሜያቸው ከ18 ዓመት በቻች የሆኑ ህጻናት በወላጆቻቸው አማካኝነት መቆጠብ የሚችሉበት የቁጠባ ሂሳብ ነው (7% ወለድ ይከፈልበታል)።

የሳጥን ቁጠባ

በሥራ ቦታ ወይም በቤት በሳጥን የሚቆጠብ የቁጠባ ዓይነት ነው (7% ወለድ ይከፈልበታል)።

የዊጆ/ድሮ ቁጠባ

ሴቶች ወይም ወንዶች ካላቸው ነገር ላይ ለ6 ወር ከቆጠቡ በኋላ በቁጠባቸው መጠን 20% ተጨምሮ ቁጠባቸው ሳይወጣ በዋስትና ተይዞ መበደር የሚያስችል የቁጠባ ዓይነት ነው፤ በተጨማሪ ደግሞ ደግሞ ዋስትና በማቅረብ የቁጠባውን አራት እጥፍ መበደር ይችላሉ። (ለዚህም ቁጠባ 8% ወለድ ይከፈልበታል)።
    1. የግል ብድር ለነጋዴዎች በቤትና በመኪና ዋስትና
    2. የባጃጅ መግዣ ብድር 50% ብድር በመቆጠብ ግማሹን ደግሞ ድርጅቱ በመክፈል ከዐሥራ አምስት ቀን በሁዋላ ገዝቶ ይሰጣል
    3. የሠራተኛ ብድር (የደመወዝ ዋስትና ብድር)
    4. ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር
    5. የዊጆ ድሮ ብድር
    6. የግብርና ብድር
የብድር አገልግሎቶችየዋስትና አይነትየብድር መጠን በብርየብድሩን ወርሃዊ ቁጠባ የቆጠበየብድሩን አጠቃላይ ቅድሚያ ቁጠባ የቆጠበ
የግል ብድርመኪና፣ ቤት፣ የባንክ አክሲዮንከ100,000 ጀምሮ 0.5%10%
የሠራተኞች ብድርየደመወዝ ዋስትና፣ የባንክ አክሲዮንበደመወዝ እስኬል መሠረት (የደመወስ 1/3ኛው ተሰልቶ)0.5%5%
የጥቃቅን እና አነስተኛ ብድርየደመወዝ፣ የቤት፣ የባንክ አክሲዮን፣ የርስበርስ ዋስትናእስከ 20,0001%10%
የዊጆ ድሮ ብድርየቁጠባ ዋስትና፣ የደመወዝ ዋስትና፣ የባንክ አክሲዮንከ20,000 ጀምሮ0.5%10%
የግብርና ብድርየርስ በርስ ዋስትናከ8,000 -30,00025 ብር10%

መግለጫ

  • ለብድር የሚከፈለውን የወለድ መጠን ወደ ተቋሙ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  • መኪናን እንደ ዋስትና ለማስያዝ መኪናው ከ1995 ወዲህ የተመረተ መሆን አለበት፤ በተጨማሪም በብሔራዊ ባንክ መኪናውን ለማስመዝገቢያ 50 ብር ይከፈላል።

የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አድራሻ

ቅርንጫፎችአድራሻስልክ
ዋና መሥሪያ ቤትመካኒሳ፣ ኤስ ሳራ (S.SARA) ታወር፣ 1ኛ ፎቅ011 3699915፣ 011 3698894፣ 011 3698998
መርካቶመሳለሚያ (ኳስ ሜዳ ማዞሪያ)፣ ሸዋጸጋ ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ 011 8277818
ገፈርሳ ኖኖአሽዋ ሜዳ፣ ብርሀኑ ሚደቅሳ ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ011 2601997
ሰበታሰበታ፣ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ አዲሱ ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ011 3662739
ወሊሶወሊሶ ከተማ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ011 36988994
መቂመቂ ከተማ፣ አዋሽ ባንክ ያለበት ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ011 3698894 / 011 3698998

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …