በጉባኤው ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለድርሻ የተገኙበት እንደነበረ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳየች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በጉባኤው የክልሉ ኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ክልላዊ ምክር ቤት አደረጃጀትና አመራር ረቂቅ መመሪያ አፀድቋል።
በውይይቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የከተማ ስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ቡልቻ በቀረበው ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት ተሰጥቶበት እንዲፀድቅ በጠየቁት መሰረት በጉባኤው ተሳታፊዎች እና በክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት አስተያየት ተሰጥቶበት የቀረበው ረቂቅ መመሪያ በጉባኤተኞች እንዲጸድቅ ተደርጓል።
ዜና እና ምስል ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ