telegram

ቴሌግራም (Telegram) እና ቢዝነስ

ቴሌግራም (Telegram) በአገራችን በጣም ተወዳጅ የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፕ/መተግበሪያ ነው። ተወዳጅ ከሆነበት ምክንያት አንዱ በአነስተኛ ዳታ መጠቀም መቻሉ ነው። ቴሌግራምን በስልካችንም ሆነ ከስልካችን አካውንት ጋር አገናኝተን በኮምፒውተራችን ላይ መጠቀም እንችላለን።

ቴሌግራም በተለይ አገራችን ውስጥ ከሌሎች የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፖች/መተግበሪያዎች በላቀ ሁኔታ ተወዳጅ ስለሆነ ለለቢዝነሶች ከፍተኛ ጥቅም አለው።

ቢዝነሶች በነኝህ መልኮች ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

  1. ቴሌግራም ቻነል በመፍጠር  

    ቴሌግራም ላይ አካውንት ያለው ሰው ቻነል መፍጠር ይችላል። የመጀመሪያዎቹን 200 ተከታዮችም ያለምንም እገዳ ከኮንታክቶቹ ላይ በማስገባት ተከታይ (Subscriber) ማድረግ ይችላል። ከ200 በላይ የሆነውን ግን ለኮንታክቶቹ መልዕክት በመላክ ተከታይ (Subscriber) እንዲሆኑ መጋበዝ ይችላል። ዋናው ነገር ቻነል መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን በሚገባ አገልግሎቶቹን ወይም ምርቶቹን በየጊዜው በመለጠፍ ለተከታዮቹ ማስተዋወቅ ነው። ተወዳጅ የሆነ ምርት ወይም አግልግሎት ካለው እና አቀራረቡ ሳቢ ከሆነ በቀላሉ ብዙ ተከታዮች ይኖሩታል።

  2. ቴሌግራም ቻት ግሩፕ  በመፍጠር

    ይሄ ከቻነል የሚለየው አባላቱ መወያየት የሚችሉበት ሲሆን ሌላ ሰውም የ ግሩፑ አባል እንዲሆን ማስገባት ይችላሉ። የግሩፑ አድሚኖች ተገቢ ያልሆነ ነገር እየተለጠፈ እንዳልሆነ መከታተል እና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

ቴሌግራም ቦት (bot)

ቴሌግራም ቦት (bot) በሶፍትዌር የሚሠራ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፊቸሮች ያሉት የቴሌግራም አካውንት ሲሆን፤ ቦትን ከቻነላችን ወይንም ከቻት ግሩፓችን ጋር በማቀናጀት የተለያዩ ሥራዎችን እንዲሠራልን ማድረግ እንችላለን።

ቴሌግራም በቀላሉ ቢዝነሳችንን የምናስተዋወቅበት መንገድ ስለሆነ ሳንውል ሳናድር https://telegram.org/ ላይ በመግባት መጠቀም መጀመር አለብን።

ይህንንም ይመልከቱ

email-business

ኢሜይልን እንዴት አድርገን ለቢዝነስ መጠቀም እንችላለን?

በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል …