peace-mfi-logo

ፒስ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

ፒስ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. በአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1164/2012 እና አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሠረት በተሰጠው ፈቃድ ቁጥር MIF/012/2014 እ.ኤ.አ ሐምሌ 1999 የተቋቋመ ሲሆን ቅድሚያ ለሴቶች የሚሰጥ የማይክሮ ፋይናንስ ኩባንያ ነው።

ፒስ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ራዕይ እና ዝርዝር መረጃ

ራዕይ

የመሥራት አቅም ያላቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ በተለይም ሴቶችን ዘላቂነት ባላቸው ሥራዎች አማካኝነት ራሳቸውን ችለውና ድህነት ተቀንሶ ማየት ነው።
ፒስ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. በኢትዮጵያ 32 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ሁሉንም ቅርንጫፎች ከዋናው መሥርያ ቤት ጋር በኮር ባንኪንግ ሲስተም በማገናኘት በቀልጣፍና ፈጣን መስተንግዶ እየሠራ ይገኛል። በተጨማሪም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የቴሌብር አገልግሎት ዋና ወኪል በመሆን ደንበኞችን በፒስ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. ቅርንጫፍ ቢሮዎች ለቴሌብር አገልግሎት በመመዝገብ የኦላይን ግብይት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያገዘ ይገኛል።

ፒስ ማይክሮፋይናንስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው?

በፈቃድ ላይ የተመሠረተ ቁጠባ (Voluntary Saving)

በፈቃድ ላይ የተመሠረተ ቁጠባ ስንል ደንበኞች በፈቃዳቸው ከ50 ብር ጀምረው በመቆጠብ 8% የሚታሰብላቸው የቁጠባ ዓይነት ነው።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ (Time Deposit)

የጊዜ ገደብ ቁጠባ ስንል ደንበኞች ቤት ለመሥራት፣ መኪና ለመግዛትና ለመሳሰሉት አቅደው የሚቆጥቡትና ጠቀም ያለ ወለድ የሚያገኙበት የቁጠባ ዓይነት ነው። የጊዜ ገደብ ቁጠባ ለመክፈት ዝቅተኛው የብር መጠን 10,000 ብር ነው። የጊዜ ገደብ ቁጠባ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት የሚቆጠብና እንደየቁጠባ መጠኑና እንደቆይታ ጊዜው ከ8.5% እስከ 13% ወለድ የሚታሰብበት ቁጠባ ነው። ከታች በሰንጠረዥ የተቀመጠውን ይመልከቱ።
የብር መጠንየጊዜ ቆይታየሚያስገኘው ወለድ መጠን
ከብር 10,000 እስከ ብር 100,0006 ወር8.5%
ከብር 10,000 እስከ ብር 100,00012 ወር9%
ከብር 100,001 እስከ ብር 500,0006 ወር9%
ከብር 100,001 እስከ ብር 500,00012 ወር10%
ከብር 500,001 እስከ ብር 1,000,0006 ወር10%
ከብር 500,001 እስከ ብር 1,000,00012 ወር11%
ከብር 1,000,000 በላይ 12 ወርእንደ ቁጠባ መጠን በድርድር የሚወሰን ሆኖ ከ 12% እስከ 13% ወለድ ይከፍላል።

ለነገ የህፃናትና ወጣቶች የፍላጎት ቁጠባ (Lenege Children and Youth)

የለነገ የወጣቶች ቁጠባ እድሜያቸው ከአንድ ቀን ጀምሮ እስከ 29 ዓመት የሆኑ ህፃናትና ወጣቶች የፍላጎት ቁጠባ ነው። ይህን ቁጠባ ለመጀመር ዝቅተኛው የብር መጠን 20 ብር ነው። ቁጠባ ለመጀመር ወላጅ ወይም አሳዳጊ የልጁን የልደት ሰርተፊኬት ማምጣት ይጠበቅበታል። ህጻናቱ ወይም ወጣቱ ለቆጠቡት ብር 8% ወለድ ይታሰብላቸዋል።

የሳጥን ቁጠባ (Box Saving)

ይህ የቁጠባ ዘዴ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲቆጥቡ የቁጠባ ሳጥን ይሰጣቸዋል። የሳጥን ቁጠባ ለመጀመር ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን 200 ብር ሲሆን ደንበኞች በቆጠቡት የሳጥን ቁጠባ 8% ወለድ ይታሰባል።

የልዩ ዝግጅት ቁጠባ (Special Event Saving)

የልዩ ዝግጅት ቁጠባ ዝቅተኛው ከ1,000 ብር ጀምሮ በየወሩ በቋሚነት የሚቆጠብ ነው። ይህ ቁጠባ በደንበኛውና በተቋሙ መካከል በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ስምምነት ሆኖ ዝግ ቁጠባ ነው። የጊዜ ስምምነቱ 6 ወር እና ከዚያ በላይ ሆኖ 9% ወለድ ይታሰባል።

ልዩ የህፃናት ቁጠባ (Special Purpose Saving for Children)

እድሜያቸው ከአንድ ቀን ጀምሮ እስከ 18 ዓመት ለሆኑ ህጻናት የሚቆጠብ ሆኖ በየዓመቱ 9% ወለድ ይታሰባል። ይህ ቁጠባ የህጻኑ እድሜ 18 ዓመት እስኪሞላ ድረስ የቆጠቡትን ገንዘብ ወጭ ማድረግ አይቻልም። የህፃኑ እድሜ 18 ዓመት ከመድረሱ በፊት የቆጠቡትን ገንዘብ ወጪ ማድረግ ከፈለጉ የሚያገኙት የወለድ መጠን 8% ይሆናል። ዝቅተኛው የቁጠባ መክፈቻ ብር 1,000 ነው።

ወለድ አልባ ቁጠባ (Interest Free Saving)

ይህ ቁጠባ ወለድ ለማይፈልጉ ደንበኞች ያለወለድ ገንዘባቸውን በኩባንያው የሚቆጥቡበት አገልግሎት ነው።

ግብርና ለሆኑ የሥራ ዘርፎች

ለበግና ፍየል እርባታ፣ ለበሬ ግዥ፣ ለከብት ማደለብ፣ ለምርጥ ዘር ግዥ፣ ለማዳበሪያ ግዥ፣ ለወተት ላሞች ግዥ ወዘተ የተመቻቹ ብድሮች ናቸው።

ግብርና ላልሆኑ የሥራ ዘርፎች

  • ለጥቃቅን ንግድ ሥራዎች፦ ለውበት ሳሎን፣ ለእጅ ባለሙያ ሠራተኞች፣ ለምግብና መጠጥ ሥራና ለመሳሰሉት ለጥቃቅንና መካከለኛ ንግድ ሥራዎች እንዲሁም በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ለተሠማሩ በግልና በቡድን የሚሰጥ ብድር
  • የሴቶች ኢንተርፕራይዝ ልማት ፕሮግራም (WEDP)ብድር
  • የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር (SME)ብድር
  • የታዳሽ ኃይል ብድር
  • ንጹህ ታዳሽ ኃይል የሶላር ብድር በቴክኖሎጂ የታገዘ የክፍያ ሥርዓት ያለው

ፒስ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. አድራሻ

ዋና መሥርያ ቤት

ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 03፣ የቤት ቁጥር 198፣ ከመስቀል ፍላወር ሆቴል በስተጀርባ

ስልክ ቁጥር

  • +251 11 557 0420
  • +251 11 557 0923
  • +251 11 470 1402
  • +251 11 652 1541

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ፒስ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …