ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። የሥራ ፈጣሪዎች በአንድነት የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉም የተቋቋመ ማሕበር ነው፡፡
ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር፦ አገልግሎቶች
- በሕግ ወይም በፍርድ መብቱ ያልታገደ
- እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ
- የማኅበሩን ዓላማ፣ ደንብና መመሪያ የተቀበለ
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና ሁለት 3*4 ጉርድ ፎቶ
- የመመዝገቢያ፦ ብር 500
- መደበኛ ወርሃዊ ቁጠባ፦ ብር 500
- የአንድ እጣ ዋጋ ብር 100 ሲሆን ዝቅተኛውን የእጣ መጠን 50 እጣዎች (ሼር) በብር 5000 መግዛት የሚችል
- መደበኛ ቁጠባ
- የፍላጎት ቁጠባ
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ
- ወለድ የማይታሰብለት ቁጠባ
- የልጆች ቁጠባ
- የትምህርት ቁጠባ
- አዲስ ንግድ ለመጀመር የሚሰጥ የብድር አገልግሎት
- የነበረ ንግድ ለማስፋፋት የሚሰጥ የብድር አገልግሎት
- የአስቸኳይ ጊዜ ብድር ለህክምና
- የአስቸኳይ ጊዜ ብድር ለጨረታ
- የአስቸኳይ ጊዜ ብድር ለሰርግ እና ወዘተ
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በመጠቀም የገበያያ ትስስር መድረኮችን ማመቻቸት
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ዌብሳይት እና ቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ምርት የማስተዋወቅ አገልግሎት መስጠት
- የሥልጠና አገልግሎት
- የማማከር አገልግሎት
- አነስተኛ የብድር የህይወት መድህን አገልግሎት
- የልምድ ልውውጥ መድረኮች ማመቻቸት
ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ:- አድራሻ
- የቢሮ አድራሻ፦ ካሳንቺስ፣ ነጋ ሲቲ ሞል፣ 3ኛ ፎቅ ከኦዳ ሕንጻ አጠገብ፣ ኢንተርፕረነርሽፕ ማሠልጠኛ ማዕከል ውስጥ
- ስልክ ቁጥር፦ +251 90 06 71 699፣ +251 90 06 71 700
- ድረ-ገጽ፦ habeshaentreprenurssacco.com
- ኢሜይል፦ habeshaentrepreneurs2011@gmail.com
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።