ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኀብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 985/2009 ሲሆን፤ ሕጋዊ ሰውነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኀብረት ሥራ ኤጀንሲ በነሐሴ 2005 ዓ.ም. ፈቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል።
“ቤተል ውስጥ ሁላችንም አለን!!”
ቤተል በቀዳሚነት የሚንቀሳቀሰው ለአባላት አክሲዮን ከመሸጥ እና ከመደበኛ ቁጠባ የሚገኘውን ገንዘብ በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ፣ የዳበረ ማኅበራዊ ግንኙነት እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በአባላትና በማኀበሩ እንዲኖር ማድረግ ነው።እንዲሁም ማኀበረ ሰቡን በገንዘብ አስተዳደር አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥ ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ ማኀበር ነው።
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የኀ/ሥ/ማኀበር:- ራእይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ
ራእይ
የተለወጠ ባሕል ያለው የኢኮኖሚ ማኀበረ ሰብ ተፈጥሮ ማየትተልዕኮ
የሀገራችንን ኀብረተ ሰብ በማስተባበር፣ ዘመኑ በፈቀደው ሥልጣኔ በመጠቀም፣ የአባላቱን የገንዘብ ቁጠባ እና አቅርቦት አስተማማኝ ማድረግዓላማ
ከአባላቱ ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ፣ ለአባላትና ለሕብረት ሥራ ማኅበራት ብድር በመስጠት፣ ማኅበሩ ጠንካራ የፋይናንስ አቋም እንዲኖረው በማስቻል የኢንቨስትመንት አቅምን መፍጠር- የቁጠባ ባሕል በማሳደግ የአባላትን በራስ የመተማመን አቅም ማጎልበት
- በአባላት ዘንድ ገንዘብ የመቆጠብና የመበደር ባሕል አጎልብቶ የሥራ ፈጠራን ማስፋፋት
- አባላት ያላቸውን ዕውቀት፤ ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት
- አስተማማኝ ባንክ ነክ አገልግሎቶችን መስጠት
- ለአባላት የተለያዩ ሥልጠናዎችን ማመቻቸት
- እገዛ የሚያስፈልጋቸውን የኀብረተ ሰብ ክፍሎች በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማገዝ
- አባላትን በከፍተኛ ቁጥር በመጨመር የማኅበሩን የማበደር አቅም ማሳደግ
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ የሚሠጣቸው አገልግሎቶች
- መደበኛ ቁጠባ
- የፈቃደኝነት ቁጠባ
- የልጆች፣ የታዳጊ ቁጠባ
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ
- የትምህርት ቁጠባ
- የቢዝነስ ቁጠባ
- ለሥራ ማስኬጃ (የገቢ ማስገኛ)
- የፍጆታ ብድር
- የትምህርት ብድር
- ለሕክምና ብድር
- ለመድኅን ዋስትና ብድር
- የቋሚ ንብረት ግዥና እድሳት
- የቤት እድሳት ብድር እና ሌሎች ለየተለያየ ዓላማ የሚውሉ የብድር ዓይነቶች
- መገዛት የሚገባውን እጣ የገዛ እና በተከታታይ የቆጠበ
- መበደር የሚፈልገውን ገንዘብ መጠን 30% የቆጠበ
- ለጠየቀው ብድር ተመጣጣኝ የሰው፣ የንብረት፣ የዕጣ ዋስትና ማቅረብ የሚችል
- የማኅበሩን ዐላማ እና ደንብ የተቀበለ
- ዝቅተኛውን ክፍያ የሚከፍል፤ ማለትም 5 ዕጣ የሚገዛ። አንዱ ዕጣ ብር 500 ሲሆን፣ ዐምስቱ ደግሞ 2500 ብርነው። ስለዚህ ዐምስቱን ዕጣ መግዛት የሚችል
- ተጨማሪ የመመዝገቢያ ብር 210 ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
- በየወሩ ብር 210 የግዴታ ቁጠባ ለመቆጠብ የተስማማ
የቁጠባ ወለድ
- ለግዴታ ቁጠባ፦ 8% ወለድ
- የፈቃደኝነት ቁጠባ ከግዴታ ቁጠባ የተሻለ ወለድ አለው፤ በስምምነትም ይወሰናል
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ፦ 9% ወለድ
- የህጻናት ቁጠባ፦ 9% ወለድ
የብድር ወለድ
- የብድር ወለድ፦ 12% ያስከፍላል
- የራስ የሆነ ድርጅት ባለቤት መሆን
- የትርፍ ተካፋይ መሆን ያስችላል
- የገንዘብ ፍላጎትን በቀላሉ መፍታቱ
- ገንዘብ ለመበደር የራስዎን ድርጅት እንጂ የሰው እጅ እና ፊት አያዩም
- የቁጠባ ባሕልዎን በቀላሉ ያሳድጋሉ
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ
ቤተል ሰፈር ከሚገኘው ቤተል ፖስታ ቤት፣ አቢሲያ ባንክ ፊትለፊት
ስልክ
- 0912 354695
- 0923 712927
- 0913 256721
ዘወትር ይቆጥቡ፣ ለቁም ነገር ይበደሩ!
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።