facebook-business-page

ፌስቡክ እና ቢዝነስ

ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ፌስቡክን በቀላሉ ቢዝነስን ለማሳደግ መጠቀም ስለሚቻል የተጠቃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ለቢዝነሶች ጥሩ ዕድል ነው።

ፌስቡክን ለቢዝነስ መጠቀም የሚቻልባቸው መንገዶች፦

  • የድርጅታችንን ወይንም የፌስቡክ ገጽ መፍጠር
  • ጓደኞቻችን እና የእነሱ ጓደኞች፣ የጓደኞቻቸው ጓደኞች፣ ወዘተ ገጻችንን እንዲከተሉ መጋበዝ
  • የድርጅታችንን ምርቶች፣ ዜናዎች፣ አዳዲስ ዕድሎች፣ ወዘተ በየጊዜው መለጠፍ
  • ለሚመጡ አስተያየቶች፣ መልዕክቶች፣ ወዘተ አስፈላጊ የሆነ መልስ መስጠት
  • ከድርጅታችን ቀጥታ ከተገናኙ ነገሮች በተጨማሪ ከቢዝነሳችን ጋር በቀጥታ ያልተገናኙ ግን የተያያዙ ነገሮችን (ዜናዎች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች) መለጠፍ፣ ማጋራት
  • ገጻችን ላይ ከቢዝነስ ውጭ የሆኑ እና አጨቃጫቂ ነገሮችን፣ ያልተረጋገጡ ዜናዎችን፣ ወዘተ አለመለጠፍ
  • ያልሆኑ ነገሮችን ኮመንት ላይ የሚጽፍ ሰውን ብሎክ ማድረግ
  • ሴኪዩሪቲውን በደንብ የተጠናከረ ማድረግ፣ ያለ አድሚን ፈቃድ ገጽ ላይ እንዳይለጠፍ ማድረግ

facebook

  • የግል ህይወታችንን ተሳስተን እንኳን የቢዝነስ ገጻችን ላይ አለማጋራት
  • በአንጻሩ ግን በቢዝነስ ገጻችን ላይ የምንለጥፈውን ነገር የግል ገጻችን ላይ ማጋራት
  • የቢዝነስ ስልክ ቁጥራችንን ገጻችን ላይ ማስቀመጥ
  • ባይ ሴል (Buy Sell) ግሩፕስን መቀላቀል እና ምርታችንን ወይንም አገልግሎታችንን ማጋራት
  • ለፌስቡክ ገጻችን የምንሰጠው የቢዝነሳችንን ወይንም የምርታችንን ስም መሆን አለበት
  • ስንጽፍ ፊደል አለመግደፍ፣ ግልጽ በሆነ ቋንቋ መጻፍ
  • የምንለጥፋቸው ጽሑፎች ምስል ቢኖራቸው የበለጠ ተመራጭ ይሆናል፣ ስለዚህ ሁሌም ትክክለኛ እና ከሌላ ያልተወሰደ ምስል ማጋራት
  • የግድ አስፈልጎን ያልተከለከለ (copy righted ያልሆነ) ምስል ወይም ጽሑፍ ከሌላ ቦታ ብንወስድ፣ ምንጭ መጥቀስ
  • የምርታችንን ወይንም የአገልግሎታችንን ቪዲዮ በየጊዜው መለጠፍ፣ ማጋራት

ለተጨማሪ:- https://www.facebook.com/business/pages/set-up ማየት ይቻላል።

ይህንንም ይመልከቱ

email-business

ኢሜይልን እንዴት አድርገን ለቢዝነስ መጠቀም እንችላለን?

በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል …