የጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳትና ቆዳ ኢንዱስትሪ የሰራተኞች ማህበር ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ አደረገ።
ዘርፉን ከማሳደግ ጎን ለጎን አሁን ላይ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ19 ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ ባሉ ፋብሪካዎች የጤና እና የደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ማከናወንም የዘመቻው አላማ ነው ተብሏል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ በኮቪድ19 ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብም ሆነ ፋብሪካዎችን ባትዘጋም ተቀባይና ገዢ ሃገራት እንዲሁም ኩባንያዎች ትዕዛዝ መቀነሳቸው ዘርፉ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
እነዚህ ኩባንያዎች አሁን ላይ ወደ ስራ እየተመለሱ ከመሆኑ አንጻርም ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ምርቶቻቸውን መላክ ይጀምራሉም ብሏል።
ከዚህ አንጻርም ፌዴሬሽኑ ዘርፉን ማሳደግ በሚያስችል መልኩ የፋብሪካ ሰራተኞች የተሻለ የንጽህና አጠባበቅ እንዲኖራቸው እንደሚሰራም ገልጿል።
ምንጭ:- ፋና ቢሲ (Fana BC)