ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ፌስቡክን በቀላሉ ቢዝነስን ለማሳደግ መጠቀም ስለሚቻል የተጠቃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ለቢዝነሶች ጥሩ ዕድል ነው።
ፌስቡክን ለቢዝነስ መጠቀም የሚቻልባቸው መንገዶች፦
- የድርጅታችንን ወይንም የፌስቡክ ገጽ መፍጠር
- ጓደኞቻችን እና የእነሱ ጓደኞች፣ የጓደኞቻቸው ጓደኞች፣ ወዘተ ገጻችንን እንዲከተሉ መጋበዝ
- የድርጅታችንን ምርቶች፣ ዜናዎች፣ አዳዲስ ዕድሎች፣ ወዘተ በየጊዜው መለጠፍ
- ለሚመጡ አስተያየቶች፣ መልዕክቶች፣ ወዘተ አስፈላጊ የሆነ መልስ መስጠት
- ከድርጅታችን ቀጥታ ከተገናኙ ነገሮች በተጨማሪ ከቢዝነሳችን ጋር በቀጥታ ያልተገናኙ ግን የተያያዙ ነገሮችን (ዜናዎች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች) መለጠፍ፣ ማጋራት
- ገጻችን ላይ ከቢዝነስ ውጭ የሆኑ እና አጨቃጫቂ ነገሮችን፣ ያልተረጋገጡ ዜናዎችን፣ ወዘተ አለመለጠፍ
- ያልሆኑ ነገሮችን ኮመንት ላይ የሚጽፍ ሰውን ብሎክ ማድረግ
- ሴኪዩሪቲውን በደንብ የተጠናከረ ማድረግ፣ ያለ አድሚን ፈቃድ ገጽ ላይ እንዳይለጠፍ ማድረግ
- የግል ህይወታችንን ተሳስተን እንኳን የቢዝነስ ገጻችን ላይ አለማጋራት
- በአንጻሩ ግን በቢዝነስ ገጻችን ላይ የምንለጥፈውን ነገር የግል ገጻችን ላይ ማጋራት
- የቢዝነስ ስልክ ቁጥራችንን ገጻችን ላይ ማስቀመጥ
- ባይ ሴል (Buy Sell) ግሩፕስን መቀላቀል እና ምርታችንን ወይንም አገልግሎታችንን ማጋራት
- ለፌስቡክ ገጻችን የምንሰጠው የቢዝነሳችንን ወይንም የምርታችንን ስም መሆን አለበት
- ስንጽፍ ፊደል አለመግደፍ፣ ግልጽ በሆነ ቋንቋ መጻፍ
- የምንለጥፋቸው ጽሑፎች ምስል ቢኖራቸው የበለጠ ተመራጭ ይሆናል፣ ስለዚህ ሁሌም ትክክለኛ እና ከሌላ ያልተወሰደ ምስል ማጋራት
- የግድ አስፈልጎን ያልተከለከለ (copy righted ያልሆነ) ምስል ወይም ጽሑፍ ከሌላ ቦታ ብንወስድ፣ ምንጭ መጥቀስ
- የምርታችንን ወይንም የአገልግሎታችንን ቪዲዮ በየጊዜው መለጠፍ፣ ማጋራት
ለተጨማሪ:- https://www.facebook.com/business/pages/set-up ማየት ይቻላል።