መነሻ / የቢዝነስ ዜና / ሚድሮክ ኢትዮጵያ 5 ሊትር ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች አቀረበ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ 5 ሊትር ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች አቀረበ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ። መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ቀረጥ ከማንሣቱ ጋር ተያይዞ፣ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች እየሸጠ እንደሚገኝም ገልጿል።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር በቀለ ጎላዶ እንዳሉት፣ መንግስት የሸማቶችን የኑሮ ጫና በመጋራት በማንሣቱ፣ ሚድሮክም በአነስተኛ የትርፍ እዳግ የምግብ ዘይቱን አቅርቧል።

አሁን ላይ የምግብ ዘይቱን በአዲስ አበባ በሚገኙት አራት ኩዊንስ ሱፐርማርኬቶች ለተጠቃሚዎች እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል – ዶክተር በቀለ።

ወደ አገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት ለሸማቶች እንዲዳረስ በሚል፣ አንድ ሸማች ከሁለት ባለ አምስት ሊትር ዘይት በላይ መግዛት እንዳይችል መደረጉም ተወስቷል።

የምግብ ዘይት በአገር ውስጥ ለማምረት ሚድሮክ ፋብሪካ እየገነባ መሆኑን ያስታወሱት የንግድ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈፃሚው፣ ፋብሪካው እስኪጠናቀቅ ድረስ የምግብ ዘይት ምርቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀርብ ይደረጋል ብለዋል።


የዜና ምንጭ፦ የፋና ቢሲ ድረ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …