መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የክልል ታርጋ ያላቸው ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ተወሰነ
motorcycle

የክልል ታርጋ ያላቸው ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የክልል ታርጋ ያላቸው ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ወሰነ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ስጦታው አካለ በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ታርጋ ካላቸው የሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ውጭ ሌሎች ወደ መዲናይቱ መግባትም ሆነ በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በተሰሩ ስራዎች እና በተከናወኑ ግኝቶች የክልል ታርጋ በመለጠፍ እንደ ዝርፊያ ካሉ ትንንሽ ወንጀሎች እስከ ከባድ ወንጀሎች በሞተር ሳይክሎች ይፈጸሙ ነበር ተብሏል።

የክልል ታርጋን ተገን በማድረግም ታርጋውን ህጋዊ እውቅና የሌለው እና አስመስሎ በመስራት ወንጀሎቹ ሲፈፀሙ እነደነበር ያነሱት የቢሮ ሀላፊው መዲናይቱ ካለባት የትራንስፖርት መጨናነቅ በላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መበራከት ለውሳኔው ምክንያት መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ባለፉት ሁለት እና ሶስት ሳምንታትም የክልል ታርጋ የለጠፉ በርካታ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች መያዛቸውንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ 15 ሺህ ያህል ሞተር ሳይክሎች ይንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ሃላፊው አሁን ላይ ህጋዊ ፈቃድ ያገኙ እና ህግን ተከትለው ፈቃድ ማግኘት የቻሉት ከ3 ሺህ 600 እንደማይበልጡት ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህ በትራንስፖርት ባለስልጣን የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት እና ህጋዊ ፈቃድ በማግኘት በ56 ማህበራት ውስጥ ሆነው እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ ይዘውት የነበረው ታርጋ ህጋዊ ያልሆነ፣ ህጋዊ እውቅና የሌላቸው በአጠቃላይ ህገወጥ ሆነው የተገኙ በመሆናቸው ወደ ስራ መግባት አልቻሉም ብለዋል።

ከዚህ በኋላ በመዲናይቱ የኮድ ሁለትም ይሁን ኮድ 3 የሁለት እግር ተሽከርካሪ ፈቃድ እንደማይሰጥም አስረድተዋል፡፡

የዜና ምንጭ፦ የፋና ቢሲ ድረ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …