መነሻ / የቢዝነስ ዜና / ከፍታ ማዕከል በስዊድን እና ኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ተጎበኘ
kefta-april-delegates-visit

ከፍታ ማዕከል በስዊድን እና ኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ተጎበኘ

ሐሙስ መጋቢት 30፣ 2013 ዓ.ም የከፍታ ማዕከል ከስዊድን እና ከኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች፣ እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዑክ የመጡ ጎብኚዎችን አስተናግዷል። ጉብኝቱ የተካሄደው የከፍታ አጋር በሆነው የኔዘርላንድስ በጎ አድራጎት ድርጅት ኤስኤንቪ (SNV) እና ከሴቶች እና ወጣቶች ጋር በተያያዘ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊዌይ (LI-WAY) አስተባባሪነት ነው።

delegates-visit-kefta

በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ለንድክዊስት፣ በኔዘርላንድስ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ታይስ ዉድስትራ፣ እንዲሁም ሌሎች የየኤምባሲዎቹ እና የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቡድን አባላት ስለ ሥራው ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ከፍታ በአዲስ አበባ ብሎም በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለሥራቸው የሚጠቅም መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ የታለመ ማዕከል ነው። በከፍታ አገልግሎት፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቱመርካቶ (2merkato.com) የሚያወጣቸው በመላ ኢትዮጵያ የሚወጡ የጨረታ ማስታወቂያዎችን ያገኛሉ፤ እንዲሁም ምርት እና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር ይፈጠርላቸዋል።

ከፍታ አገልግሎቱን ለማሳለጥ በድረ ገጽ፣ በሞባይል መተግበሪያ እንዲሁም በጥሪ ማዕከል ኢንተርፕራይዞችን በማገልገል ላይ ይገኛል። በተጨማሪም፣ የከፍታ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ ደንበኞችን በሰፊው ለመድረስ በታሰበው “መግቢያ” መተግበሪያ ላይ ሥራቸውን የማስተዋወቅ ዕድል ያገኛሉ። በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ደግሞ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ ማሽነሪ እና ሠራተኛ ክፍያ ወቅታዊ ዋጋ በሚያቀርበው እና የኮንስትራክሽን ሥራ ትስስር በሚፈጥረው የኮንስትራክሽን ፖርታል (con.2merkato.com) ላይ ጭምር ሥራቸው ይተዋወቃል።

በከፍታ ማዕከል እስከ አሁን ድረስ ሦስት ሺሕ ያህል ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዓመታዊ ደንበኝነት እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …