ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉባቸው በየአካባቢው የሚደረጉ ባዛሮች በሚከተለው መልኩ ይካሄዳሉ።
የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች የሚያዘጋጁዋቸው ባዛሮች
አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አሥሩ ክፍለ ከተማዎች፣ በዓመት አራት ጊዜ ባዛሮችን ያዘጋጃሉ። ባዛሮቹ በአጠቃላይ በተከታዩ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሚደረጉ ናቸው፡-
- የዘመን መለወጫ በዓል ሰሞን
- የገና በዓል ሰሞን
- የፋሲካ በዓል ሰሞን
- ክፍለ ከተማው የተሻለ ነው የሚለው አንድ ተጨማሪ ወቅት
በባዛሮች የሚሳተፉት የትኞቹ ኢንተርፕራይዞች ናቸው? ዓላማውስ ምንድነው?
የአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሚያዘጋጃቸው ባዛሮች
ከሁሉም ክልሎች የተመረጡ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉባቸው ሁለት ባዛሮች በቢሮው አዘጋጅነት በየዓመቱ ይካሄዳሉ። እንዚህ ባዛሮች (እንደ ሌሎቹ) በዋናነት የቴክኖሎጂ ልምድ ልውውጥና ኢንተርፕራይዝ ለኢንተርፕራይዝ ትስስር መፍጠርን ዒላማ ያደረጉ ሲሆኑ፣ የሚዘጋጁበት ጊዜ እንደ ሁኔታው በቢሮው የሚወሰን ነው።
በባዛሮች እንዲሳተፉ የሚጋበዙ ኢንተርፕራይዞች በአምራችነት ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ፣ ባዛር ላይ ይዘው መቅረብ የሚችሉትም ራሳቸው ያመረቱትን ምርት ብቻ ነው።
በባዛር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑትም በምርታቸው ወይም በአሠራራቸው የተሻሉ ናቸው ተብለው የተመረጡ ናቸው።
ባዛር የሚዘጋጅበት ዓላማ በዋናነት ኢንተርፕራይዞች እርስ በርስ ትስስር እንዲፈጥሩና አንዳቸው ከሌላቸው የቴክኖሎጂ ልምድ እንዲለዋወጡ ነው።