አሸንጎ ኢቨንትስ እና ቤተ-ሰማይ ክሪኤቲቭ ሚዲያ፣ በኤስኤንቪ፣ ሊዌይ እና ሲዳ ትብብር “የነገው ባዛር” የተሰኘ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ባዛር አዘጋጅተዋል።
በባዛሩ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞች በሚል አሸንጎ ኢቨንትስ የላከልን ሙሉ መረጃ ይህን ይመስላል።
“የነገው ባዛር” ዓላማ
የነገው ባዛር ዓላማ አገር የሚያኮራ ሥራ የሚሠሩ የሥራ ፈጣሪዎችን፣ ከአገር ወዳድ እና ጥራት አድናቂ ሸማቾች ጋር በማገናኘት የገበያ ዕድል መፍጠር ነው። ይህም ዘና በሚያደርግ እሁድ ቀን የሚካሄድ ነው።
ማን መሳተፍ ይችላል?
- በቆዳ ምርት
- በጨርቃ ጨርቅ
- በባሕል አልባሳት
- በምግብ እና መጠጥ
- በእጅ ሥራ እና ጌጣጌጥ
ዘርፎች የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በባዛሩ መሳተፍ ይችላሉ።
የት እና መቼ ይካሄዳል?
ቦታው፦ እስጢፋኖስ አቅራቢያ በሚገኘው በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል (Hyatt Regency Hotel)
ቀኑ፦ በየወሩ እሁድ (የአሁኑ ዙር እሁድ፣ ግንቦት 8፣ 2013 ዓ.ም ይካሄዳል)
ብሳተፍ ምን እጠቀማለሁ?
- ገበያዎን ያሰፋሉ
- አዳዲስ ሸማቾችን ያገኛሉ
- ስለ ባዛር አቀራረብ ሥልጠና ይወስዳሉ
- “ለደንበኛ ምርጥ” ሽልማት ይወዳደራሉ (በሽልማቱ ንግድዎን/ሥራዎን ያሳድጋሉ)
ከእኔ ምን ይጠበቃል?
- ሥራዎን/ንግድዎን የማሳደግ ፍላጎት እና ተነሣሽነት
- የመመዝገቢያ ቅጹን መሙላት (ቅጹን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል)
- ተመርጠው የባዛሩ ተሳታፊ ከሆኑ ለሚይዙት ጠረጴዛ 1,000 ብር ክፍያ ማዘጋጀት
ለበለጠ ማብራሪያ የባዛሩን አዘጋጆች በስልክ +251 96 288 7277 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።