መነሻ / Uncategorized / ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.
debo-mfi

ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.

ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክስዮን ማኅበር የተቀላጠፈ የማይክሮፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ለባለአክሲዮኖች ትርፍ ለማስገኘትና የደንበኞችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል የተቋቋመ ተቋም ነው። ማኅበሩ በቀዳሚነት የተቀላጠፈና ውጤታማ የሆነ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ማቅረብ ዓላማው ያደረገ አክስዮን ማኅበር ነው።

በአሁኑ ወቅት ደቦ ማይክሮፋይናንስ አዳዲስ አከባቢዎችና ማኅበረሰቦች ጋር በቀጣይነት ለመድረስና የተበዳሪዎችንና የተበዳሪ ቤተሰቦችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል የተሻለ የብድር አገልግሎት እያቀረበ ይገኛል።

ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አገልግሎቶቹን ለማኅበረሰቡ ለማድረስ የተለያዩ መንገዶችን የሚከተል ሲሆን ከተወጠነበት ጊዜ ጀምሮ የተቀመጡ ዕሴቶችን በመጠቀም የኢኮኖሚ ልማት ለማነቃቃት እንዲሁም ሠራተኞቹን በዘላቂነት በማነሳሳት ዕለታዊ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ደቦ የሚሰጣቸው የቁጠባ አይነቶች
  • የውዴታ ግዴታ ቁጠባ
  • ቅድመ ብድር ቁጠባ
  • በየወሩ የሚከፈል ቁጠባ
  • የፈቃደኝነት ቁጠባ
  • የጊዜ ገደብ ተቀማጭ
ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አገልግሎቱን ለማስፋትና የደንበኞቹን ፍላጐትና እርካታ ለማሟላት ሁለት ዋና ዋና የብድር አሰጣጥ ዘዴዎችን በመጠቀም የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት እያቀረበ ይገኛል።
  1. በቡድን፦ በአንድ አካባቢ የሚገኙ እንዲሁም ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር ያላቸው በጥቃቅን ንግድና ግብርና ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ከሦስት እስከ አምስት በሚሆን የቡድን አባል በመደራጀት የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
  2. በግል፦ የግል ብድር ተጠቃሚ ደንበኞች በአንጻራዊነት የተሻለ የብድር መጠን የሚያገኙ ሲሆን በቂ የብድር ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ደቦ በዋናነት የሚከተሉትን የብድር አገልግሎቶች ይሰጣል።
  • በቡድን ዋስትና የሚሰጥ የንግድ ሥራ ብድር
  • ግብርና ሥራ በቡድን ዋስትና የሚሰጥ ብድር
  • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ብድር
  • ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ብድር
  • የቤት ቁሳቁስ መግዣ ብድር
  • የሠራተኛ ደመወዝ ብድር እና ልዩ ብድር
  • በንብረት ዋስትና - መኪና ወይም የቤት ካርታ
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
  • በደመወዝ ዋስትና - ለባለ ትዳር የጋብቻ ሰርተፊኬት
  • ንግድ ፍቃድ
  • ላላገባ 6 ወር ያልሞላው ሰርተፍኬት
  • ሁለት ጉርድ ፎቶ
  • የብድሩን መጠን  3% የአገልግሎት ክፍያ እና 2% የህይወት ዋስትና (በብድሩ ጊዜ ተበዳሪ ቢሞት ዋስትና)
  • ቅድመ ቁጠባ ከፍያው የሚፈጸመው ከብድሩ ላይ ሲሆን ክፍያው የሚፈጸመው ደግሞ ብድሩ በሚወሰድበት ጊዜ ነው
  • የደብተር መግዣ 15 ብር
የብድር ጣሪያ በብርየወለድ መጠንየውሉ ጊዜ
13500015.83%ለ1 ዓመት
ደቦ ዋና መሥርያ ቤት እና ቅርንጫፎችስልክ
ቦሌ ቲኬ ሕንጻ አንደኛ ፎቅ011 6721518/19/20
ሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ011 1712356
ኦሮሚያ ክልል ፣ መቂ ከተማ022 1182097
ሀዋሳ ከተማ046 2120795

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክሲዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

business-to-business

የገበያ ትስስር

እዚህ ላይ የተመዘገቡ ኢንተርፕራይዞችን ዝርዝር፣ ሥራቸውን፣ የድርጅታቸውን ፕሮፋይል እና አድራሻቸውን በመጠቀም አብሮ መሥራት ይቻላል።