እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ የተቋቋመ ሲሆን ዋናው ቢሮውም በኮልፌ አጠና ተራ ይገኛል።

እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር:- ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶች

ራዕይ

በ2035 ዓ.ም. ዘላቂነት ያለው ማኅበራዊ የገንዘብ ተቋም ፈጥሮ የበለጸገ ትውልድን ማየት

ተልዕኮ

ኅ ብረተሰብን ቁጠባ በማስተማር እና በማሳተፍ አስተማማኝነት ያለው ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት

ዕሴቶች

  • ራስን በራስ መርዳት
  • የግል ኃላፊነትን መወጣት
  • ወንድማማችነት
  • ፍትሐዊነት
  • እኩልነት

እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር:- የሚሠጣቸው አገልግሎቶች

  • የመደበኛ ቁጠባ
  • የፈቃደኛ ቁጠባ
  • ልዩ የፈቃደኝነት ቁጠባ
  • እስከ ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ድረስ
  • ተመጣጣኝ ወለድ (10%-13%)
  • የኢንሹራንስ አገልግሎት
  • የሥልጠና አገልግሎት
  • የምክር አገልግሎት እና ሌሎች
  • የማኅበሩን ዓላማና ደንብ የሚያከብር
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
  • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
  • የመመዝገቢያ ክፍያ 600 ብር መክፈል
  • መደበኛ ቁጠባ በየወሩ 350 ብር መቆጠብ
  • ቢያንስ የአንድ አክስዮን (ሼር) 1000 ብር ኢንቨስትመንት መጀመር
  • በድምሩ በመጀመሪያ ጊዜ 1950 ብር መክፈል የሚችል

እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር:- አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

አዲስ አበባ፣ ኮልፌ አጠና ተራ፣  ሰማሁ ሆቴል አጠገብ ባለው ዘውዲቱ ፕላዛ ሕንጻ ሥር፣ ቢሮ ቁጥር 081/G-11

ፌስቡክ ገጽ

እስታቴር ገንዘብ ቁጠባና ብድር stater saving and credit

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …