መነሻ / የቢዝነስ ዜና / ሸገር ዳቦ በ400 ማከፋፈያዎች እየተሰራጨ ነው ተባለ

ሸገር ዳቦ በ400 ማከፋፈያዎች እየተሰራጨ ነው ተባለ

የሸገር ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በ400 ማከፋፈያዎች ለአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሲሳይ ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፣ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ዳቦዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች ማሰራጨት ጀምሯል።

ፋብሪካው በዋነኛነት የዳቦ ዋጋን የኅብረተሰቡን ገቢ ባገናዘበ አነስተኛ ዋጋ የማቅረብ ዓላማን ይዞ እንደመግባቱ ተደራሽነቱ ላይ በጥብቅ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በግብይት ሂደቱ ሰንሰለቱን በማሳጠር በመሀል የሚገባ ደላላን ለመከላከል በራሱ ተሽከርካሪዎች እያከፋፈለ ይገኛል ነው ያሉት – ዋና ሥራ አስኪያጁ።

በፋብሪካው የተመረተው ዳቦ በከተማዋ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ በሆኑ የተመረጡ ቦታዎች በከተማ አስተዳደሩ በተደራጁ ወጣቶች አማካኝነት አቅርቦቱ መቀጠሉንም ተናግረዋል።

የሸገር ዳቦ አሁን ላይ በቀን 600 መቶ ሺህ ዳቦ እያመረተ ለአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች እያሰራጨ ሲሆን፥ በቀጣይም በሙሉ አቅሙ ለማምረት ዕቅድ ይዟል።

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በቀጣይ እስከ 2 ሚሊየን ዳቦ በቀን የማምረት አቅሙን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ፣ በቀን እስከ 2 ሚሊየን ዳቦ የማረት አቅም ያለው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ሰኔ 18፣ 2012 ዓ.ም በይፋ መመረቁ ይታወሳል።


የዜና ምንጭ፦ የፋና ቢሲ ድረ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …