ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማኅበረ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመቆጠብ የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት፣ በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ሥራ አመራር ሃሳብ አመንጪነት እና በሠራተኞች መሥራችነት ጥቅምት 5 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ።
ግሬት! ለእድገት ጽኑ መሠረት!
ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ ራእይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ
ራእይ
በመላው ኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ የማኅበረ ሰቡን ኑሮ የሚለውጥ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ሆኖ ማየትተልዕኮ
አባላትን በማስተባበር ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በአባላት ፍላጎት ላይ በተመሠረተ መልኩ በሃገራችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ላይ የድርሻውን በመወጣት ለአባላቱ የተሻለ የቁጠባ፣ የብድር እና ሌሎች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ የኑሮ ደረጃቸውን ማሻሻልዓላማ
- ዘላቂነት ያለው ቀልጣፋ የገንዘብ ተቋም መፍጠር
- አባላት በኅብረት ሥራ ማኅበራቸው ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኑሮአቸውን ማሻሻል
- ለአባላት ፈጣን እና ተአማኒነት ባለው መንገድ የብድር አገልግሎት መስጠት
- ማኅበረ ሰቡ የሚያገኘውን ገቢ በአግባቡ እንዲጠቀምበት ስለቁጠባ ባሕል ትምህርት መስጠት
- የትርፍ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
የቁጠባ ሕጋግት
- የማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ሲሆን ይህን ቁጠባ ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል።
- እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል።
- አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ይወስዳል።
- ነገር ግን ተጨማሪ የቆጠበውን የፍላጎት ቁጠባ አስገዳጅ በሆነ ጊዜ ወጪ አድርጎ መጠቀም ይችላል።
የቁጠባ ዓይነቶች
- መደበኛ ቁጠባ
- የፍላጎት ቁጠባ
- የልጆች ቁጠባ
- የበዓል ወጪ ቁጠባ
- የጉዞ ቁጠባ
- የሕክምና ቁጠባ
- ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ቁጠባ
- አንድ አባል ብድር ማግኘት የሚችለው የቆጠበውን አራት እጥፍ ነው። ለዚህም መውሰድ የሚፍልገወን መጠን 25% መቆጠብ ይኖርበታል።
- የተበደረውን ገንዘብ በ24 ወራት ከፍሎ ለሚጨርስ 12% ወለድ ይከፍላል።
- በ36 ወራት ከፍሎ ለሚጨርስ 13% ወለድ ይከፍላል።
- በ48 ወራት ከፍሎ የሚጨርስ 14% ወለድ ይከፍላል።
- የብድር አገልግሎት ለማግኘት ብድር ፈላጊው ቢያንስ ለተከታታይ 6 ወራት መቆጠብ አለበት
- የገቢ መግለጫ ማቅረብ አለበት
- ለብድሩ ተመጣጣኝ ዋስትና ማቅረብ አለበት
- የጋብቻ ሁኔታን የሚገልጽ ሰርተፍኬት መቅረብ አለበት
- ዋስ በአካል መቅረብ ይኖርበታል
- የራስንና የዋስን የጋብቻ አጋር (ባል ወይም ሚስት) በአካል ማቅረብ ያስፈልጋል
- ከጠቅላላ ብድሩ 1% የብድር መድኅን እና 1% ደግሞ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል አለበት
- በቁጠባ ዋስትና
- በደመወዝ ዋስትና
- በአባል ዋስትና
- በንብረት ዋስትና
- ለመኪና እና ለቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስ ይሆናል
- የባንክ አክሲዮን ዋስትና
- ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪው የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ እና ባቀረበው የዋስትና መጠን ብቻ ነው።
- ት/ቤት መሄድ ያልቻሉ ሕፃናትን የትምህርት ድጋፍ መስጠት
- አረጋውያን አቅመ ደካሞችን መርዳት
- የሕክምና ድጋፍ ማድረግ
- ሀገራዊ ልማቶች እና በመንግሥት ድጋፍ ሲጠየቅ መሳተፍ፤ ለምሳሌ፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ ችግኝ ተከላ ወዘተ...
- የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ሲሆን አንድ አባል መግዛት የሚችለው ዝቅተኛው 1 ዕጣ ብር 1,000 ነው።
- ከፍተኛው መግዛት የሚችለው ደግሞ 200 ዕጣ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ነው።
- በአዲስ አበባና በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ነዋሪ የሆነ እና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
- ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሠርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
- በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመሪያ ተገዥ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ
- በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
- በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተወሰነውን የመመዝገቢያ ክፍያ የገንዘብ መጠን መክፈል የሚችል
- አባል ለመሆን መግዛት የሚያስፈልገውን የዕጣ መጠን በአንድ ጊዜ መክፈል ወይም 1/3 ኛውን ከመመዝገቢያ ጋር ከፍሎ ቀሪውን 2/3 በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ክፍሎ ማጠናቀቅ የሚችል
- ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም
ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ
አድራሻ
መገናኛ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ግሬት ኮሚሽን ሚንስትሪ ኢትዮጵያ የወንጌል ተልዕኮ ማዕከል ሕንጻ ግራውንድ ፍሎርስልክ
- 0118 68 39 90
- 0979 62 05 85
- 0911 90 44 96
- 0911 88 09 33
- 0947 34 76 36
ኢሜይል
greatsavingassociation@gmail.comማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።