መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ቆንጆ ማስታወቂያ
konjo-advertising

ቆንጆ ማስታወቂያ

ድርጅቱ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም በወይዘሮ ቆንጂት አይፎክሩም እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የማስታወቂያ እና ጠቅላላ የሕትመት ሥራዎችን ይሠራል። ይህ ድርጅት በኅትመት ሥራ የስድስት ዓመት የሥራ ልምድ አለው።
የሚሰጣቸው አገልግሎቶች (ምርቶች)

  • ብሮሸር
  • ካላንደር
  • መጽሔት
  • ቢዝነስ ካርድ
  • ባነር
  • ቲሸርት
  • ማኅተሞች
  • መጽሐፍ
  • ፍላየር
  • አጀንዳ እና
  • አጠቃላይ የኅትመት ሥራዎችን በጥራት ይሠራል።

 

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

የድርጅቱ መሥራች አባል የግላቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት በኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተቀጥረው ይሠሩ ነበር። ይህንንም ሥራ ትምህርታቸውን እየተማሩ በትርፍ ጊዜያቸው ነበር የሚሠሩት። በመቀጠል ትምህርታቸውን ሲጨርሱ በሶፍት ዌር ዴቭሎፕመንት ሥራ ተቀጥረው ሠርተዋል። ሥራውም ለቢሮዎች ኮምፒውተራይዝድ የሆነ ሲስተም መፍጠር እና የኔትወርክ ሲስተም መዘርጋት ነበር። በዚህም አጋጣሚ የወ/ሮ ቆንጂት አለቃ ስለ ሥራው አሠራር ያስተምሯቸው ነበር፤ እንዲሁም በራሳቸው እንዲጀምሩ ይገፋፏቸው ነበር።

ወ/ሮ ቆንጂት ሁለቱንም ሥራዎች እየሠሩ በነበረበት ጊዜ የግል ሥራ እንዴት መሠራት እንዳለበት በብርቱ ያስቡበት ነበር። እሳቸው የራሳቸውን የኅትመት ሥራ ለመሥራት የመረጡበት ምክንያት የኅትመት ሥራ የሚሠሩ ጓደኞች ስለነበሩዋቸው ነው። ሥራው እንዴት እንደሚሠራ በማየት እንዲሁም ኢንተርኔት ካፌ በሚሠሩበት ጊዜ ንዳንድ የካርድ ኅትመት ሥራ ትእዛዞች ይመጡ ስለነበር እነዚህን ሥራዎች ለመሥራት ስለሚፈልጉ ጓደኞቻቸው ጋር በመሄድ በደንብ እየተማሩ ሥራውን ተገነዘቡ። ሥራውን እየወደዱትና እያወቁት ሲመጡ የራሳቸውን ድርጅት ቆንጂት፣ ሰናይት  እና ጓደኞቻቸው የኅትመት ሥራ ኅብረት ሽርክና ማህበር መሥርተዋል። ይህም ራሳቸው ሠርተው ራስን ለመለወጥ እና ብሎም የሌሎችን ህይወት መቀየር እንዲችሉ ረድቷቸዋል። ቆንጆ ማስታወቂያ ሲመሠረት የነበረው መነሻ ካፒታል ሃያ ስምንት ሺህ ብር ነበር። አሁን በሊዝ የገዛቸው ትልልቅ ማሽኖችን ጨምሮ ወደ ሰባት መቶ ሺህ ብር ካፒታል ደርሷል።

ድርጅቱ A6 ሦስት ሺህ ደረሰኞችን በሃያ ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ አቅም አለው። ምንም ዓይነት የኅትመት ሥራ ቢመጣ ከአምስት እስከ ሃያ ቀን የጊዜ ገደብ ውስጥ የማጠናቀቅ አቅም አለው። ይህ ድርጅት ለስድስት ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር ችሏል፤ እንዲሁም ሥራ ሲበዛ ለሚመጡ አምስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ሲሆን ይህም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎችን ይከታተላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርብ ጊዜ በከፈቱት ቢሮ ቀጥታ የሚመጡ ሥራዎችን ይሠራሉ፤ እንዲሁም ቢዝነስ ካርድ በመበተን ሥራዎችን ይሠራሉ።

የኅትመት ሥራ ላይ ከሚፈጠሩ ችግሮች መካከል የገበያ እና የፋይናንስ ችግሮች ዋናዎቹ ናቸው። እንዲሁም የኅትመት ማቴሪያል እጥረት ለዋጋ መናር ዋና ምክንያት ሲሆን በመቀጠልም የማሽን መበላሸት ከሚከሰቱ ችግሮች የሚጠቀሱት ናቸው። እነዚህን ችግሮች በመመካከር እና ረጋ ብሎ በማጤን መፍትሔ በመፈለግ እና ሥራ ላይ በማዋል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ተፅዕኖ በጣም ከባድ ነበር፤  እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ የነበረው አለመረጋጋት ገበያው ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት አድርሷል። ይህም ሥራ እንዲቀንስ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ሥራ አላቆሙም፤ ሠራተኞችን በመቀነስ በትንሹም ሲንቀሳቀሱ ነበር። አሁን ሥራው ትንሽ እየተሻሻለ ይገኛል ብለዋል የድርጅቱ መሥራች። ይህም ተከትሎ ገበያው ወደድሮው እየተመለሰ ይገኛል።

ምክር እና እቅድ

ወደ ኅትመት የሥራ ዘርፍ የሚገባ አዲስ ሰው ትዕግስተኛ፣ ቻይ፣ ተግባቢ የማይደክመው እና የማይሰልች ለመማር ፈቃደኛ የሆነ የሰዎችን ሀሳብ መቀበል የሚችል ሰው መሆን አለበት። እንዲሁም ቴክኖሎጂን በሚገባ የሚጠቀም መሆን አለበት፤ ይህም ራስን ለማሳደግ እና የተለያዩ ዘመናዊ አሠራሮችን ለመማር እና ለማወቅ ይጠቅማል። የሚፈልጉትን ቢዝነስ በደንብ ማጥናት አስፈላጊ ነው። ቢዝነስ ሲጀምሩ ኪሳራ እንዳለው አምነው ራሳቸውን ዝግጁ አድርገው ቢገቡ ጥሩ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድርጅቱ ወደ ፊት አሁን ያለውን የማሽን እዳ ከፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ ሌሎች ማሽኖችን የመጨመር እና ጥሬ እቃ በብዛት የመያዝ እና በማከማቸት የመሥራት አቅሙን ለማሳደግ እቅድ አለው።

2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት ፓኬጅ ለአንድ ዓመት በነጻ ተጠቅመዋል። ጥቅሙንም በማየት የቀጣዩን የአንድ ዓመት ክፍያ በመክፈል አገልግልቱን በቀጣይ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።  በከፍታ የምክክር ስብሰባ ላይ በመገኘታቸው የማስታወቂያን ጥቅም በሚገባ በመረዳታቸው ወደ ፊት የማስታወቂያውን አገልግሎት በሚገባ መጠቀም እንደሚጀምሩ ጠቅሰዋል።

ወ/ሮ ቆንጂት ስለከፍታ አገልግሎት የሚከተለውን ብለዋል “የጨረታ ሥራን ለመሥራት በከፍታ ፓኬጅ ነው የምንቀሳቀሰው አሁን አቅም እየጎደለን ቢኖር ተሳትፈን ምን እናደርገዋለን ብለን ነው እንጂ ያለ ጨረታ ኅትመት ከባድ ነው። አሁን ባለው የጥሬ እቃ ችግር ምክንያት ራሱ ሁለት ጨረታዎችን አሸንፈን ዋጋ በጣም በመወደዱ  መልሰናል። ስቶክ ላይ እቃ ከሌለ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ካለው የጥሬ እቃ አርቦት ችግር እንጻር ከባድ ፈተና እየሆነ ነው እንጂ ጨረታ በጣም ጠቅሞናል ስለዚህ ለዚህ በተቻለ መፍትሔ መፈለግ  ተገቢ ነው” ብለዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …