በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱ ይታወሳል።
የከተማ አስተዳደሩ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሲያከናውን የነበረውን የማጥራት ሥራዎችን ማጠናቀቅ ተችሏል። በመሆኑም ተጥሎ የነበረው እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የተነሳ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
የዜና ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ የፌስቡክ ገጽ