LinkedIn - Business

ሊንከዲን (LinkedIn) እና ቢዝነስ

ሊንከዲን (LinkedIn) በማይክሮሶፍት ባለቤትነት የተያዘ ለቢዝነሶች፣ ለፕሮፌሽናሎች፣ ለሥራ ፈላጊዎች እና ቀጣሪዎች የተቋቋመ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ነው።

አባል ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። ግን የአባልነት ዓይነቱን ወደ ፕሪሚየም (premium) ከፍ ማድረግ ከፈለግን እና ማስታወቂያ ማውጣት ከፈልግን ግን ከፍያ ያስከፍለናል። ከዚህ በታች የተጠቀሱት አግልግሎቶች በሙሉ በነጻ ናቸው።

linkedin-business

ቢዝነሶች እንዴት አድርገው በሊንከዲን (LinkedIn) መጠቀም ይችላሉ?

    1. የቢዝነሱ ባለቤቶችም ሆነ ተቀጣሪዎች የሊንከዲን ፕሮፋይል እንዲኖራቸው ማድረግ።
    2. ለቢዝነሱ ራሱን የቻለ ገጽ (page) መፍጠር
    3. በየጊዜው ስለቢዝነሱ አገልግሎቶች፣ ምርቶች፣ ኹነቶች (events)፣ አዳዲስ ነገሮች መለጠፍ። የሚለጠፉት ነገሮች በሙሉ በጥሩ መንገድ (በኢንግሊዝኛ ወይንም አማርኛ) መጻፍ አለባቸው።
    4. የቢዝነሱ ባለቤቶች እና ተቀጣሪዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ኮኔክት (connect) ማድረግ እና ኮኔክሽኖችን ማብዛት
    5. እንኝህን ኮኔክሽኖች የቢዝነሱን ፔጅ ተከታይ እንዲሆኑ መጋበዝ፤ ሊንከዲን በየወሩ አንድ መቶ (100) ያህል ክሬዲቶችን በመስጠት ኮኔክሽኖቻችንን እንድንጋብዝ ያስችለናል። የተጋበዙት ኮኔክሽኖች ፔጃችንን ከተከተሉ፣ ክሬዲቱ ሳይቃጠል ይመለስልናል።

ሊንከዲንን በድረ ገጹ ወይንም በሞባይል አፕ (በአንድሮይድም ሆነ በአይፎን (iOS)) ማግኘት ይቻላል። ሳንውል ሳናድር ሊንከዲንን እንጠቀም። ቢዝነሳችንን ለማሳደግ እና ኔትወርክ ለመፍጠር ይረዳናል። ድረ ገጹ ይሄ ሲሆን https://www.linkedin.com/፣ ለመመዝገብ ስልክ ቁጥራችንን ወይንም ኢሜይል አድራሻችንን ማስገባት በቂ ነው!

ይህንንም ይመልከቱ

email-business

ኢሜይልን እንዴት አድርገን ለቢዝነስ መጠቀም እንችላለን?

በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል …